በሴቶች የዓለም ዋንጫ ስዊድን አውስትራሊያን በማሸነፍ 3ኛ ደረጃ ያዘች
የዘንድሮ የሴቶች የዓለም ዋንጫ ጨዋታ፣ ብራዚል እና ጀርመንን የመሳሰሉ ትላልቅ ብሔራዊ ቡድኖች በጊዜ በመሰናበታቸው ያልተጠበቀ ክስተት አስተናግዷል
ሰዊድን የዘንድሮውን የአለም ዋንጫ ተባባሪ አዘጋጅ የሆነችውን አውስትራሊያን በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች
ሰዊድን የዘንድሮውን የአለም ዋንጫ ተባባሪ አዘጋጅ የሆነችውን አውስትራሊያን በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።
ስዊድን በውደድሩ የነሀስ ሜዳሊያ ማግኘት የቻለችው በቢርሴን በተካሃደው ጨዋታ አውስትራሊያን 2 ለ0 በማሸነፍ ነው።
ጨዋታው በተጀመረ በ28ኛው ደቂቃ በቅጣት ምት ጎል ማግኘች የቻሉት ስዊድኖች አንድ ሰአት ሲሆነው የስዊድኗ አምበል ኮሶቫሬ አስላኒ ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ሆና ባስቆጠረቻት ጎል በእጥፍ መምራት ችለዋል።
የአውስራሊያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈቱን ለመቀበል ቢቸገርም ይህ ውጤት ታሪኩ እስከ ሩብ ፍጻሜ መድረስ የነበረውን የቡድኑን ታሪክ ቀይሮታል። ቡድኑ ቢሸነፍም ወደ ግማሽ ፍጻሜ መድረስ ችሏል።
በነገው እለት እንግሊዝ እና ስፔን ለዋንጫ ይፋለማሉ።
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ለሴቶች ብሔራዊ ቡድን 200 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ለመስጠት ቃል ገብተዋል።
የዘንድሮ የሴቶች የዓለም ዋንጫ ጨዋታ፣ ብራዚል እና ጀርመንን የመሳሰሉ ትላልቅ ብሔራዊ ቡድኖች በጊዜ በመሰናበታቸው ያልተጠበቀ ክስተት አስተናግዷል። በሌላ በኩል ብዙ ግምት ያልተሰጣቸው የሞሮኮ አይነት ቡድኖች ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ታይተዋል።