ብራዚላዊው ሪቻርልሰን በመቀስ ምት ያስቆጠራት ግብ የዓለም ዋንጫው ምርጥ ጎል ተብላ ተመረጠች
172 ጎሎች የተቆጠሩበት የአለም ዋንጫ በአንድ ጨዋታ በአማካይ 2 ነጥብ 7 ጎሎች ተስተናግደውበታል
ፊፋ 10 እጩ ተፎካካሪዎችን ይፋ ያደረገ ሲሆን ሪቻርልሰን ጎል ተመርጣለች
በኳታር አስተናጋጅነት በተካሄደው የፊፋ 2022 የዓለም ዋንጫ ብራዚላዊው ሪቻርልሰን በመቀስ ምት ያስቆጠራት ግብ ምርጥ ጎል ተብላ ተመረጠች።
ባሳለፍነው እሁድ በተጠናቀቀው የፊፋ 2022 የዓለም ዋንጫ 64ቱ የኳታር የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች 172 ጎሎችን አስተናግደዋል።
በጨዋታ በአማካይ 2 ነጥብ 7 ጎሎች የተሰተናገዱበት የአለም ዋንጫ በጎል የታጀበ አስደናቂ ፉክክር የታየበት መሆኑን ተመልክተናል።
ከ172 ጎሎቹ ውስጥ የምርጦች ምርጧ የትኛዋ ናት የሚለውን የመለየቱ ስራ ሲከናወን የቆየ ሲሆን በዚህም ብራዚላዊው ሪቻልሰን ያስቆጠረሰግ ጎል የምርጦች ምረወጥ መሆን ችላለች
ብራዚላዊው ሪቻርልሰን በምድብ የመጀመሪያ ፍልሚያ ላይ ሰርቢያ ላይ በ62ኛው ደቂቃ መሪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሯል። ከ11 ደቂቃ በኋላ ያስቆጠራት ሁለተኛ የመቀስ ምት ማራኪ ጎልም አንደኛ ሆናለች።
የሳዑዲአ አረቢያው ሳሌም አል ዳውሳሪ በአርጀንቲና ላይ ፣ የኔዘርላንድሱ ኮዲ ጋክፖ በኢኳዶር ላይ፣ የአርጀንቲናው ኢንዞ ፈርናንዴዝ በሜክሲኮ ላይ፣ የካሜሮኑ ቪሰንት አቡበከር በሰርቢያ ላይ፣ የሜክሲኮ ልዊስ ቻቬዝ በሳኡዲ አረቢያ ላይ ስቆጠሯቸው ጎሎች ለአጩነት ቀርበው ነበር።
በከፍተኛ ግብ አግቢነት የወርቅ ዋንጫን የተሸለመው የፈረንሳዩ ኪሊያ ምባፔ በፖላድ ላይ፣ የደቡብ ኮሪያው ፓይክ ሲኡንግ ሆ ብራዚል ላይ እንዲሁም ብራዚላዊው ኔይማር ክሮሽያ ላይ ያስቆጠራት ጎል በእጩነት ከቀረቡት ውስጥ ይገኛሉ።