ስፖርት
የእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ጆርጅ ኮኸን በ83 ዓመቱ ህይወቱ አለፈ
ኮኸን በፈረንጆቹ 1966 የዌምብሌይ የዓለም ዋንጫን ባሸነፈው ቡድን ውስጥ የተጫወተ ነው
ሙሉ የክለቡን ቆይታ ከፉልሃም ጋር ያሳለፈው ኮኸን ለእንግሊዝ 37 ጨዋታዎችን አሸንፏል
የእንግሊዝ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ጆርጅ ኮኸን በ83 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የቀድሞ ክለቡ ፉልሃም አስታውቋል።
የቀኝ መስመር ተከላካዩ በፈረንጆቹ 1966 የዌምብሌይ የዓለም ዋንጫን ባሸነፈው ቡድን ውስጥ የተጫወተ ሲሆን በፍፃሜው ምዕራብ ጀርመንን 4 ለ 2 ሲያሸንፉ ምክትል አምበል ነበር።
ሙሉ የክለቡን ቆይታውን ከፉልሃም ጋር ያሳለፈው ኮኸን ለእንግሊዝ 37 ጨዋታዎችን አሸንፏል።
"ፉልሃም እግር ኳስ ክለብ በድንቅ ተጫዋቹ ህልፈ በጣም አዝኗል" ሲል ክለቡ ተናግሯል።
ኮኸን በእንግሊዝ ስኬታማ የዓለም ዋንጫ ዘመቻ በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ ተሳትፏል ተብሏል።
በፈረንጆቹ ከ1956 እስከ 1969 በፉልሃም ለ13 ዓመታት በተጫወተበት ጊዜ ኮኸን ለክለቡ 459 ጨዋታዎችን ተጫውቷል።
በፈረንጆቹ 1966 የእንግሊዝ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አልፍ ራምሴ የሀገሩ “ታላቅ የቀኝ ተመላላሽ” ሲሉ ጆርጅ ኮኸንን ገልጸውታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።ሙሉ የክለቡን ቆይታ ከፉልሃም ጋር ያሳለፈው ኮኸን ለእንግሊዝ 37 ጨዋታዎችን አሸንፏል