ግጭቱ የተከሰተው በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል እንደሆነ ተገልጿል
በስዊድን ስቶኮልም የሚኖሩ ኤርትራውያን ጎራ ከፍለው መደባደባቸው ተገለጸ።
በስዊድን ስቶኮልም በተዘጋጀ የኤርትራዊያን በዓል ላይ ሁከት ተከስቶ ሰዎች መጎዳታቸው ተገልጿል።
በስዊድን መዲና በተካሄደው በዚህ በዓል ላይ ለመሳተፍ በስፍራው ተገኝተው እያለ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ደጋ እና ተቃዋሚ ናቸው የተባሉ ኤርትራዊያን መካከል ግጭት መከሰቱን ፍራንስ 24 ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ሰባት ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል እንደገቡ ተገልጿል።
ከአንድ ሺህ በላይ እሚሆኑ ኤርትራዊያን በስዊድን የተካሄደውን በዓል ተቃውመው ወደ ስፍራው የመጡ ሲሆን ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋልም ተብሏል።
አራቱ ኤርትራውያን ክፍኛ ተጎድተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው የተባለ ሲሆን 100 ተጠርጣሪ ኤርትራውያን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።
ከአንድ ወር በፊት በጀርመን በተካሄደ ተመሳሳይ የኤርትራ ባህላዊ በዓል ላይ በተፈጠረ ሁከት 26 የጀርመን ፖሊሶች መጎዳታቸው ይታወሳል።
በዚህ በዓል ላይ ግጭት ውስጥ የገቡት የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ተከስቶ በርካታ ኤርትራዊያን ተጎድተውም ነበር።