ስዊድን በራሱ የሚንቀሳቀሰውን የመድፍ ሲስተም ለብሪታኒያ ልትሸጥ ነው
የስዊድን ጦር ዘመናዊውን "አርቸር ወይም ቀስተኛው" ሃዊትዘር ጦር መሳሪያ ባለቤት የሆነው በ2013 ነበር
ሽያጩ በተዘዋዋሪ ብሪታኒያ ዩክሬንን እንድትረዳ ሚያስችል ነው ተብሏል
ስዊድን በራሱ የሚንቀሳቀሰውን አርቸር የመድፍ ስርአት ለብሪታኒያ ልትሸጥ ነው፡፡
አርቸር ወይም ቀስተኛው መድፍ ከምርጥ የሃዊትዘር ስረአት አንዱ ሲሆን ብዙም ወድ ያልሆነ አማራጭ በመሆን ተፈላጊ ሆኖ እየመጣ ያለ የጦር መሳሪያ ነው፡፡
- የኔቶ ኃላፊ ቱርክ ስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን እንዲቀላቀሉ የምታጸድቅበት “ጊዜ አሁን ነው” አሉ
- ስዊድን እና ፊንላንድ የኔቶ አባል ለመሆን 130 “ሽብርተኞችን” አሳልፈው ሊሰጡኝ ይገባል - ቱርክ
የመሳሪያ ሽያጩ የሚከናወነው ሁለቱም ሀገራት በተስማሙት መሰረት ሲሆን ለንደን የቆየውን አይኤስ-90 የመድፍ ስርአቷን ጦርነት ላይ ላለችው ዩክሬን እንድትሰጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
የስዊድን መንግስት በመግለጫው ብሪታኒያ 14 "አርቸር ወይም ቀስተኛ" መድፎች ትገዛለች ብሏል።
ስቶክሆልም ቀስተኛውን መድፍ በቀጥታ ወደ ዩክሬን እንደምትልክ በጥር ወር በገለጸችው መሰረት አስካሁን ስምንት መድፎች እንደላከች ተረጋግጧል፡፡
በስዊድን እየተመረተ ያለው የ"አርቸር ወይም ቀስተኛው " የመድፍ ስርአት ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የሆነና በሁሉም ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የተጫነ ሃዊትዘር ነው።
መድፉ በላቁ ቴክኖሎጂዎች እና አውቶማቲክ ስርአትን በመታገዝ ከርቀት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
የስዊድን መከላከያ ሚኒስትር ፓል ጆንሰን "እንደ አርቸር የመሰለ የጦር መሳሪያ ከታጠቁ ተሽከርካሪዎች እና ታንኮች ጋር በመሆን የዩክሬንን የመከላከል አቅም የሚጨምር እና ግዛቷን መልሳ እንድታገኝ የሚያስችል" ብለዋል።
የስዊድን መንግስት እስካሁን ለዩክሬን 11.6 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ መመደቡን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ለዩክሬን ከባድ የጦር መሳሪያ ለማቅረብ ቃል የገቡትን የምዕራባውያን ሀገራት ቡድንን ባለፈው የካቲት ወር የተቀላቀለችው ስዊድን ከ"አይሪስ ቲ" እና "ሀውክ" ጸረ-አውሮፕላን ሲስተም በተጨማሪ 10 ሊዮፓርድ-2 ታንኮች እንደምትሰጥም ቃል ገብታለች፡፡
የስዊድን ጦር ዘመናዊውን "አርቸር ወይም ቀስተኛው" ሃዊትዘር ጦር መሳሪያ ባለቤት የሆነው እንደፈረንጆቹ በ2013 ነበር፡፡
የስዊድን የመድፍ ስረአት ከሌሎች የሚለየው 30 ኪሎ ሜትር የመምዘግዘግ አቅሙ ነው፡፡