ቱርክ ግንኙነታቸው የሻከረውን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን እያደራደረች መሆኗ ይታወሳል
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊደን በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሃካን ፊደን በነገው እለት አዲስ አበባ እንደሚገቡም ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሃካን ፊደን በኢትዮያ ቆይታቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አስጽቀስላሴ ጋር እንደሚወያዩም ተነግሯል።
በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሃካን ፊደን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር እንደሚገናኙም ነው የተነገረው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ኢትዮጵያ ከምጣታቸው በዘለለ በምን ጉዳይ ላይ እንደሚመክሩ በይፋ የተነገረ ነገር የለም።
ቱርክ ግንኙነታቸው የሻከረውን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ማደራደር መጀመሯ ይታወሳል።
የሰጡት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን፥ ሀገራቱ ልዩነታቸውን በሰላማዊ ንግግር ለመፍታት መስማማታቸውም አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ እና የቱርክ የሃገራቱ ዲፕሎማሲያዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት 128 ዓመታትን በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፤ ጠንካራ የንግድ ትስስር መመስረት ችለዋል።
ቱርክ በሰሜን ኢትዮጵያጦርነት ሲካሄድ ለኢትዮጵያ ድሮኖችን መሸጧ የሚታወስ ነው።