ቻይና "የታይዋን ነጻነትን" ለመቃወም የሚያሽችል ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ አድርጋለች
ታይዋን፤ ቻይና “አሮጌ አስተሳሰብን ማስወገድ አለባ” አለች፡፡
ታይፔ ይህን ያለችው ጉበኤውን ሲያካሂድ የሰነበተው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የታይዋን ነጻነትን በተመለከተ ያለውን ተቃውሞ በህገ መንግስቱ ላይ ካረጋገጠ በኋላ ነው፡፡
የታይዋን የድንበር ተሸጋሪ ፖሊሲዎች አስፈጻሚ አካል የሆነው የመይንላንድ ጉዳዮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ "የቻይና ኮሚኒስት መንግስት አዲሱ አመራር የወረራ እና የመጋጨት አስተሳሰቡን አስወግዶ ልዩነቶችን በሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና በተጨባጭ መንገድ እንዲፈቱ እንጠይቃለን" ብሏል፡፡
የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በህገ-መንግስቱ ላይ "የታይዋን ነጻነትን" ለመቃወም የሚያሽችለው ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ አድርጓል፡፡
ማሻሻያው ቅዳሜ ዕለት በፓርቲው ብሔራዊ ኮንግረስ ላይ ከ 2ሺህ በላይ ተወካዮች ያሳለፉት ውሳኔ አካል ነው መባሉን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ለአንድ ሳምንት የቆየው ይህ የኮሙኒስት ፓርቲ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግን ፓርቲውን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በሊቀመንበርነት እንዲመሩ በመምረጥ በትናንትናው እለት መጠናቀቁ ይታወቃል፡፡
የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከዚህ በተጨማሪም ቻይናን ከፈረንጆቹ 2012 ዓመት ጀምሮ በሬዝዳንትነት እየመሩ ላሉት ዢ ጂንፒንግን ተጨማሪ ስልጣንም እንደሰጠም ሽንዋ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ቻይናን ሲመሩ ከኮሙንስት ፓርቲ ጽንሰ ሀሳብ ባለፈ ለቻይናዊያን ይበጃል የሚሉትን ሀሳብ ወደ ተግባር መቀየር እንዲችሉ ፈቃድም ሰጥቷል።
ፓርቲው 25 አባላት ያሉት የፖሊት ቢሮ እና አዲስ ሰባት የማዕከላዊ አባላት የተመረጡ ሰዎችን ያሳወቁ ሲሆን በፖሊት ቢሮ አንድም ሴት አለማካተታቸው አነጋገሪ ሆነዋል፡፡
ቻይና ሴት የፖሊት ቢሮ አባል የሌለው ካቢኔ ስታዋቅር በ25 ዓመታት መጀመሪያው ነው ተብሎለታል፡፡
ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግን በፓርቲው ጉባኤ መዝጊያ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር ለቻይና ድል እንደሚዋጉ እና እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በኮሮና ቫይረስ ፣ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እየተፈተነ ያለውን ኢኮኖሚ ማስታግስ እንዲሁም የታይዋን ጉዳይ ለፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ ዋነኛ ትኩረት የሚሰጡባቸው ጉዳዮች ናቸው።