በአፍሪካ ትልቁ ተራራ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት 500 በላይ በጎ ፋቃደኖች ተሰማርተዋል
በአፍሪካ ትልቁ ተራራ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት 500 በላይ በጎ ፋቃደኖች ተሰማርተዋል
የታንዛኒያ መንግስት ሄሊኮፕተርና አውሮፕላኖችን በመጠቀም በአፍሪካ ትልቁ በሆነው የኪሊማንጃሮ ተራራ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የተፈጥሮ ሀብትና ቱሪዝም ሚኒስትር ሀምሲ ኪዋንጋላ በትዊተር ገጻቸው እንደጻፉት በኪሊማንጃሮ ብሄራዊ ፓርክ በእሳት ማጥፋት ስራ ላይ የተሰማሩትን 500 በጎ ፈቃደኞች ሊረዱ የሚችሉ የሄሊኮፕተርና አውሮፕላኖችን ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ኪግዋንጋላ እንደገለጹት የእሳቱ መስፋፋት የማጥፋት ስራውን እንዳከበደው ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሯ እንዳሉት በቦታው ያለው ጠንካራ ንፋስና ደረቅ ሳርና ደን የማጥፋቱን ስራውን ፈታኝ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
እሳቱ እስካሁን 28 ስኩየር ኪ.ሜ ቦታ የሸፈነ ደንን ያወደመ ሲሆን አሁንም ኪፉኒካ በተባለው የተራራው ክፍል እሳቱ እንደቀጠለ ነው፡፡
የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን በማጥፋት መሻሻል ያሳዩ ቢሆንም ጠንካራው ንፋስ እንደገና እሳቱን በማስነሳቱ በሰሜን ታንዛኒያ በኩል 30 ኪ.ሜ ድረስ ታይቷል፡፡ እተፋፋመ ያለው እሳት ሆሮምቦ የተባለውን የቱሪስት ካምፕ ሙሉ በሙሉ ማጥፋቱም ተገልጿል፡፡
እሳቱ ባለፈው እሁድ ሆና በተባለው የተራራው ክፍል ነበር የተነሳው፤ የእሳቱ መነሻ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም፡፡