የታንዛኒያ ምርጫ ኮሚሽን ለጥቅምቱ ምርጫ 80ሺ የምርጫ ማእከላትን አዘጋጀ
ምክትል ኮሚሽነሩ እንዳሉት እያንዳንዱ ማእከል ለ500 ሰዎች ታስቦ ተዘጋጅቷል
ኮሚሽኑ 29 ሚሊዮን ታንዛኒያውያን በዚህ አመት ምርጫ ለመምረጥ ተመዝግበዋል ብሏል
ኮሚሽኑ 29 ሚሊዮን ታንዛኒያውያን በዚህ አመት ምርጫ ለመምረጥ ተመዝግበዋል ብሏል
የታንዛኒያ ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው በመጭው በፈረንጆቹ ጥቅምት 28 ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ 80ሺ የምርጫ ማእከላት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ምባሮክ ሳሊም ምባሮለክ 79670 የሚሆኑት በዋናዋ ታንዛንያ የተዘጋጁ ሲሆን ቀሪዎቹ 485 የሚሆኑት በዛንዚባር ደሴቶች ተዘጋጅተዋል፡፡
ምክትል ኮሚሽነሩ እንዳሉት እያንዳንዱ ማእከል ለ500 ሰዎች ታስቦ እንደተዘጋጀ ጠቅሰዋል፡፡
የምርጫ ማእከላቱ ሲዘጋጁ በእድሜ የገፉ ሰዎችን፣ መስማት የተሳናቸውንና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኮሚሽኑ ኢንፎርሜሽንና የመራጮች ትምህርት ጊቭነስ አስዊሌ የምርጫ ዝግጅት በሙሉ አቅም እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
አስዋሌ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ ለምርጫ ጣቢያዎች የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ላይ መሆኑን ተነግሯል፡፡
እንደ ኮሚሽኑ 29 ሚሊዮን ታንዛኒያውያን በዚህ አመት ምርጫ ለመሳተፍ ተመዝግበዋል፤በፈረንጆቹ 2015 በነበረው ምርጫ 23 ሚሊዮን ነበር የተመዘገበው፡፡ ታንዛኒያ 57 ሚሊዮን ህዝብ አላት፡፡