በታንዛኒያ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ በሆነው ኪሊማንጃሮ ባለፈው እሁድ የተነሳው እሳት እስካሁን አልቆመም
በታንዛኒያ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ በሆነው ኪሊማንጃሮ ባለፈው እሁድ የተነሳው እሳት እስካሁን አልቆመም
በታንዛኒያ በሚገኘውና በአፍሪካ ከፍተኛ ቁመት ባለው ተራራ ላይ በላፈው እሁድ የተነሳው እሳት ተባብሶ ቀጥሎ 28 ኪ.ሜ ስኩየር የሚሸፍን ደን ማውደሙን የአካባው ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡
የታንዛኒያ ፖርኮች ጥበቃ ኮሚሽነር አላን ኪጃዚ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ለማጥፋት እየጣሩ ቢሆንም እሳቱ የሸፈነው ቦታ ከፍ ሊል እንደሚችል መናገራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ኪጃዚ እንደገለጹት እሳቱን በ24 ሰአታት ውስጥ ይጠፋል ብለው ይጠብቃሉ፡፡
ኃላፊው እንደገለጹት እሳቱ ሙሉ በሙሉ በቀጥጥር ስር ከዋለበኋላ የጠፋው እጽዋት ምን ያህል ነው ለሚለው ቆጠራ ይካሄዳል ብለዋል፡፡
በእሳት አደጋው ላይ በተከሄደው የመጀመሪያ ምርመራ በጃርኩ ውስጥ ባሉ ሰራተኞች በድንገት መነሳቱን ከኮሚሽኑ የመጡት ፓስካል ሹሉተቴ በጋዜጣዊ መግለጫው ተናግረዋል፡፡
እሳቱ መጀመሪያ የፈነዳው ተራራ ወጭዎች በሚያርፉነት የተራራው ክፍል ነው ተብሏል፡፡ በታንዛኒያ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ የሆነው ኪሊማንጃሮ ተራራ ከባህር ወለል በላይ 5895 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡