በለጋ እድሜው ኪነጥበቡን የተቀላቀለው አርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ ከ40 በላይ ፊልሞች ላይ ተውኗል
በተለያዩ የፊልም ትወናዎች ላይ እውቅናን ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
አል ዐይን አማርኛ ከአርቲስት ታሪኩ ብርሃ (ባባ) አብሮ አደጎች ባገኘው መረጃ መሰረት አርቲስት ታሪኩ ረዘም ጊዜ ህመም ላይ እንደነበረ እና ላለፉት ወራት ህክምና እየተከታተለም ነበር።
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህክምና ላይ እያለ ዛሬ ማለዳ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን የአርቲስቱ አብሮ አደጎች ነግረውናል።
አርቲስት ታሪኩ ብርሀኑ በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ተክለሀማኖት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ተወልዶ ያደገው።
ከልጅነቱ ጀምሮ በአካባቢው ባሉ የኪነ ጥበብ ማህበራት ተሳትፎን ሲያደርግ የነበረው አርቲስት ታሪኩ ገና በለጋ እድሜው በብዙ ፊልሞች ላይ ተውኗል።
በ30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ያለው አርቲስት ታሪኩ ከ40 በላይ የአማርኛ ፊልሞች ላይ በመተወን ብዙ አድናቆቶችን እና ሽልማቶችን አግኝቷል።
አርቲስት ታሪኩ ከተወነባቸው ፊልሞች መካከልም 300ሺ፣ የፍቅር ABCD ፣ ብላቴና፣ ቦሌ ማነቂያ ፣ እንደ ባል እና ሚስት ፣ ኢንጂነሮቹ ፣ እርቅ ይሁን ፣ ኢዮሪካ ፣ ጉዳዬ ፣ ሀገርሽ ሀገሬ ፣ ሕይወቴ ፣ ህይወት እና ሳቅ ፣ ከባድ ሚዛን ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ ፣ ከቃል በላይ፣ላውንድሪ ቦይ ፣ ኮከባችን ፣ ማርትሬዛ ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ ፣ ትዳርን ፍለጋ ፣ አንድ ሁለት ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ ወንድሜ ያዕቆብ ፣ እንደ ቀልድ ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ የሞግዚቷ ልጆች፣ ይዋጣልን ፣ ዋሻው፣ ወሬ ነጋሪ እና ወጣት በ97 ዋነኞቹ ናቸዉ።
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ባለትዳር እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበረ።