አንድ አመት የወሰደው የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ድርድር
በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትና ኪሳራ ለሚደርስባቸው ሀገራት ሊደረግ ስለሚገባው ድጋፍ ሲካሄድ የነበረው ድርድር በአቡዳቢ ተጠናቋል
አሜሪካ በአለም ባንክ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ተጠቃሚዎች ዙሪያ ቅሬታዋን አሰምታለች
የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ27) ባለፈው አመት በግብጽ ሲካሄድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት እና ኪሳራን የሚያካክስ ድጋፍ እንዲደረግ መስማማታቸው ይታወሳል።
ሀገራት ስለሚደረገው ድጋፍ የሚደራደርና 28 አባላት ያሉት ኮሚቴ ማዋቀራቸውም ይታወሳል።
ኮሚቴው ለአንድ አመት ሲያደርገው የነበረውን ድርድር ባለፈው ቅዳሜ በአቡዳቢ ያጠናቀቀ ሲሆን ጊዜያዊ ስምምነት ላይም ደርሷል።
በህዳር ወር መጨረሻ በዱባይ በሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ(ኮፕ28) ለምክክር ይቀርባል የተባለው ጊዜያዊ ስምምነት የአየር ንብረት ለውጥ ኪሳራና ጉዳት የሚያደርስባቸው ሀገራት የሚያገኙትን ድጋፍ ያስቀምጣል።
የአለም ባንክ በጊዜያዊነት የሚያስተዳድረው የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ምንጩ ያደጉት ሀገራት ይሆናሉም ይላል።
አሜሪካ ግን ለአየር ንብረት ለውጥ የታዳጊ ሀገራትም ድርሻ አለ በሚል የፈንዱ ገቢ ምንጭ ያደጉት ሀገራት ብቻ መሆን የለባቸውም በሚል ተቃውሞዋን አሰምታለች።
የዋሽንግተን ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንዱ የሚያዋጡ ሀገራት ሊበራከቱ ይገባል የሚለውና ባደጉት ሀገራት ብቻ አይታጠር ጥያቄ በኮሚቴው ሊቀመንበር ተቃባይነት አላገኘም ተብሏል።
በአቡዳቢ በተካሄደው 5ኛውና የመጨረሻው ዙር ድርድር የመንግስታቱ ድርጅት በ1992 የበለጸጉ ብሎ የሰየማቸው ሀገራት ለፈንዱ መዋጮ እንዲያደርጉ የተወሰነበት ነው። ጊዜያዊ ስምምነቱ በዱባዩ ጉባኤ መሪዎች ከመከሩበት በኋላ ሊጸድቅ ይችላልም ተብሏል።
የአለም ባንክ ለሚያስተዳድረው የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ የሚያዋጡ ሀገራት ጉዳይ አከራካሪነቱ ቀጥሏል።
እንደ ሲንጋፖር፣ ሳኡዲ አረቢያ እና ኳታር ያሉ ሀገራት ፈጣን እድገት በማስመዝገባቸው የበለጸጉ ሀገራትን ጎራ ተቀላቅለው ሊያዋጡ ይገባል የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።
በሻርምአልሼኩ ጉባኤ የተመረጡት 28ቱ የድርድር ኮሚቴ አባላት በየአራት አመቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ኪሳራና ጉዳት ማካካሻ ፈንዱ መዋጮ እንዲሰበሰብ ተስማምተዋል።
በዚህ ፈንድ ድሃ ሀገራት እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ እያደረሰባቸው የሚገኙ ታዳጊ ሀገራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጊዜያዊ ስምምነት ቢኖርም አከራካሪ ጉዳይ ነበር።
የበልጸጉት ሀገራት በዚህ ፈንድ መጠቀም ያለባቸው የአለማችን አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራትና ደሴቶች ብቻ መሆን እንዳለባቸው ያምናሉ።