በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚደረገ የአየር ንብረት ለውጥ ድጋፍ እየቀነሰ ነው ተባለ
የተመድ ዋና ጸኃፊ እጥረቱ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አደጋ የመዋጋት ጥረት ፈቅ አለማለቱን የሚያሳይ እንደሆነ ይረዳሉ
በማድግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚደረግ አለምአቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የፋይናንስ ድጋፍ 15 በመቶ መቀነሱን የተመድ ሪፖርት አመለከተ
በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚደረገ የአየር ንብረት ለውጥ ድጋፍ እየቀነሰ ነው ተባለ።
በማድግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚደረግ አለምአቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የፋይናንስ ድጋፍ 15 በመቶ መቀነሱን የተመድ ሪፖርት አመለከተ።
የተመድ የኢንቫይሮመንት ፕሮግራም እንደገለጸው ከሆነ ምንምእንኳን የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ በሁሉም የአለም ክፍል እየጨመረ ቢሆንም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ በአመት ከ194 እስከ 366 ቢሊዮን ዩሮ ያህል እጥረት አጋጥሟል።
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ይህ እጥረት የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አደጋ የመዋጋት ጥረት ፈቅ አለማለቱን የሚያሳይ እንደሆነ ይረዳሉ።
ኤኤፍፒ እንደዘገበው ለአየር ንብረት ቅነሳ የሚውለውን ወጭ ከፈረንጆቹ 2019-25 በእጥፍ ለማሳደግ ባለድርሻ አካላት በግላስጎው ስብሰባ ቃል ቢገቡም የፋይናንስ ከፍተቱ እየጨመረ መሆኑን ዘግቧል።
አዳፕሽን ወይም የአየርንብረት ለውጥ ቅነሳ ሀገራትን እና ህዝቦች ከአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖዎች መጠበቅ ማለት ሲሆን የፖረሱ የአየር ንብረት ስብሰባ ቀልፍ ነጥብ ነው።
በፈረንጆቹ 2009 ሀብታም ሀገራት የአለም የሙቀት መጠንን ለመቀነስ እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት በ2020 የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ 100ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር።
ነገርግን ይህ መጠን ከ83 ቢሊዮን ዶላር በላይ አለማለፉ ተገልጿል።
የተመድ የኢንቫይሮመንት ፕሮግራም በሰራው ትንተና በ2021 ለአዳፕሽን የተገኘው ድጋፍ 21.3 ቢሊዮን ዶላር ነው። ይህም በ2020 ከተሰበሰበው 25.2 ቢሊዮን ዶላር ያነሰ ሆኖ ተገኝቷል።