የውኃ ሽታ ሆኖ ከቀረ 10 ዓመታትን ስላስቆጠረው MH370 አውሮፕላን እስካሁን የምናውቀው?
በረራ ላይ እያለ የተሰወረው ቦይንግ 777-200 በርካታ ፍለጋ ቢደረግንም ደብዛው እንደጠፋ ነው
MH370 አውሮፕላን ከኩዋላ ላምፑር ወደ ቤጂንግ 239 ተሳፋሪዎችን ይዞ ከተሰወረ 10 ዓመት ሞላው
ንብረትነቱ የማሌዢያ የሆነ MH370 ቦይንግ 777-200 አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ ደብዛው ከጠፋ 10 ዓመታትን አስቆጠረ።
የማሌዢያ አየር መንገድ ቦይንግ 777-200 አውሮፕላን በወቅቱ 239 ተሳፋሪዎችን እና የበረራ አባላትን አሳፍሮ ከኳላ ላምፑር ወደ ቻይና ቤጂንግ በመብረር ላይ እያለ ነበር ደብዛው የጠፋው።
ከአውሮፕላኑ ለመጨረሻ ጊዜ የተላለፈው መልእክት ከ10 ዓመት በፊት ልክ በዛሬው እለት አውሮፕላኑን በማብረር ላይ ከነበሩት ካፒቴን ዛሂር አህመድ ሲሆን፤ ይህም አውሮፕላኑ በረራ ከጀመረ ከ40 ከ40 ዲቃ በኋላ ነበር።
“መላክም መሽት ማሌዥያውን ሶስት በሳት ዜሮ” የሚለው ቃልም ካፒቴኑ ለመረረሻ ጊዜ ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ያስተላለፉት መልእክት እንደነበረ ይታወሳል።
ከዚያ በኋላ ሁሉም ነገር ጸጥ ረጨ አለ፤ ሆኖም ግን አውሮፕላኑ ከራዳር እይታ ቢሰወርም ለሰዓታት ሲበር እንደነበረ መረጃዎች አመላክተዋል።
አውሮፕላኑ ተከስክሶ ይሆናል በሚል ግምትም በደቡብ ቻይና ባህር ላይ ፍለጋ ተጀመረ፤ በኋላም ሳተላይት አውሮፕላኑ ነዳጅ ጨሮሶ ወድቋል በሚል ጥቆማ ሰጥቷል በሚል ፍለጋው ወደ ህንድ ዉቂያኖስ ተስፋፋ።
በመቶ ሚሊየን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደረገ፤ በርካታ አይነት መርከቦችና ጀልባዎች እንዲሁም ሄሊኮፕተሮች ፍለጋው ላይ ተሰማሩ፤ ነገር ግን አንድ የአውሮፕላኑ ስብርባሪ አካል ሳይገኝ እነሆ 10 ዓመታት ተቆጠሩ።
በአውሮፕላኑ ላይ እነማን ተሳፍረው ነበረ?
በአውሮፕላኑ ውስጥ የበርካታ ሀገራት ዜጎች ተሳፍረው ነበር የተባለ ሲሆን፤ ከግማሽ በላዩ ግን የቻይና ዜጎች ነበሩ።
የቻይና አርቲስቶች፣ በሀሰተኛ የአውሮፓ ፓስፖርት ወደ ቤጂንግ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ኢራናውያን፣ ስራ ለመጀመር ወደ ቻይና ሲጓዙ የነበሩ የኢንዶኔዢያ ዜጎች እንዲሁም የሰርግ ስነ ስርዓት ላይ ቆይተው ለጫጉላ ሽርሽር ወደ ቤጂንግ ሲጓዙ የነበሩ የማሌዢያ ዜጎች በአውሮፕላኑ ተሳፍረው ነበር።
MH370 አውሮፕላንን ለመፈለግ ምን ተደረገ?
አውሮፕላኑ መጥፋቱን ተከትሎ ማሌዢያ ከሁለት ደርዘን በላይ ሀገራትን ያሳተፈ ፍለጋ በማስተባበር አካሂዳለች።
ፍለጋው ከደቡብ ቻይና ባህር የተጀመረ ሲሆን፤ በኋላ ላይ የብሪታኒያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ተቋም አውሮፕላኑ ወደ ደቡባዊ የህድ ውቂያኖስ መውደቁን ከሳተላይት መረጃ አግኝቻለው ማለቱን ተከትሎ ወዚያ ተስፋፈቶ ቀጠለ።
መጋቢት 3 በህንድ ውቂያኖስ ላይ የተጀመረው ፍለጋም 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ሜትር ስኩዌር ማካለሉም ተነግሯል።
በአጠቃላይ በሄሊኮፕተር፣ በመርከብ፣ በጀልባ እና በባህር ሰርጓጅ መርከቦች ጭምር ታግዞ የተደረገው ፍለቃ በአጠቃላይ 120 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ያካለለ ሲሆን፤ 147 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላርም ወጪ ተደርጎበታል፤ ሆኖም ግን የአውሮፕላኑ ነገር አሁንም የውሃ ሽታ እንደሆነ ቀርቷል።
የተጎጂዎች ቤተሰቦች አሁንም ቢሆን ቤተሰቦቻችን ሊገኙ ይችላሉ የሚል ተስፋን እንደሰነቁ ናቸው፤ ማሌዢያስ ከ10 ዓመታት በኋላ ፍለጋውን ዳግም ትጀምር ይሆን?...