ከዘጠኝ ዓመት በፊት የጠፋው የማሌዢያ አውሮፕላን አዲስ ፍለጋ እንዲጀመር የተጎጂ ቤተሰቦች ጠየቁ
መርማሪዎች በአውሮፕላኑ ላይ ስለተፈጠረው ነገር መደምደሚያ ላይ አልደረሱም
የአውሮፕላኑ የገባበት መጥፋት ከዓለማችን ታላላቅ የአቪዬሽን ሚስጥሮች አንዱ ነው
ከዘጠኝ ዓመት በፊት የጠፋው የማሌዢያ አውሮፕላን አዲስ ፍለጋ እንዲጀመር የተጎጂ ቤተሰቦች ጠየቁ።
የማሌዥያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ኤምኤች 370 ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የገባበት አልታወቀም።
የመንገደኛ ቤተሰቦች ኦሽን ኢንፊኒቲ የተባለ የአሜሪካ የባህር አሳሽ ኩባንያ አዲስ ፍለጋ እንዲያካሂድ የማሌዥያን መንግስት ጠይቀዋል።
የበረራ ቁጥሩ ኤምኤች 370 በአውሮፓውያኑ የዘመን ቀመር መጋቢት ስምንት 2014 ከኩዋላ ላምፑር ወደ ቤጂንግ ሲጓዝ ተሰውሯል።
የአውሮፕላኑ የገባበት መጥፋት የዓለማችን ታላላቅ የአቪዬሽን ሚስጥሮች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል።
በ2018 ማሌዢያ አውሮፕላኑን በደቡባዊ ህንድ ውቅያኖስ ላይ ለመፈለግ ለኦሽን ኢንፊኒቲ አውሮፕላኑን ካገኘ እስከ 70 ሚሊዮን ዶላር እከፍላለሁ ብላለች።
ሆኖም እንደታሰበው ጠብ ያለ ነገር አልተገኘለትም።
የኩባንያው ፍለጋ በ2017 ማሌዢያ ፣ቻይና እና አውስትራሊያ 135 ሚሊዮን ዶላር በላይ ባስወጣው የሁለት ዓመት የውሃ ውስጥ አደን የአውሮፕላኑን ዱካ ከጠፋ በኋላ ነው።
"ድምጽ 370" ተብለው የሚጠራው የመንገደኞች ቤተሰብ ስብስብ፤ ኩባንያው አዲስ ፍለጋ ለመጀመር ተስፋ እንዳለው እና የማሌዢያ መንግስት የሚቀርብለትን ሀሳብና ጥያቄ እንዲቀበል ጠይቋል።
ድርጅቱ ክፍያ የሚከፈለው ፍለጋው ከተሳካ ብቻ ነውም ተብሏል።
ሮይተርስ በጉዳዩ ላይ ኦሽን ኢንፊኒቲ እና የማሌዢያ የትራንስፖርት ሚንስቴር ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጡም ብሏል።
ነገር ግን የትራንስፖርት ሚንስትሩ አንቶኒ ሎክ በመታሰቢያው በዓል ላይ ቤተሰቦች ባስተላለፉት መልእክት የበረራውን “ዶሴውን ላለመዝጋት” ቃል ገብተዋል።
በአውሮፕላኑ ላይ “አዲስ እና አስተማማኝ መረጃ” ካለ ለወደፊት ለሚደረጉ ፍለጋዎች ተገቢ ትኩረት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
የማሌዢያ መርማሪዎች ከዚህ ቀደም በአውሮፕላኑ ላይ ስለተፈጠረው ነገር መደምደሚያ ላይ አልደረሱም። ነገር ግን አውሮፕላኑ ሆን ተብሎ ከጉዞው እንዲሰወር ተደርጓል የሚለውን ግን አልገለጹም።