ቦይንግ ኩባንያ የማክስ 737 አውሮፕላን ምርት ሀላፊን ከሀላፊነት አነሳ
ሃላፊው ከሀላፊነት የተነሱት ለ171 አውሮፕላኖች ከበረራ መታገድ ምክንያት ሆነዋል በሚል ነው
ዓለም አቀፉ የአቪየሽን ተቋም ቦይንግ ኩባንያ ከአንድ ወር በፊት ባጋጠመው የምርት እክል ምክንያት በርካታ ኪሳራዎችን እያስተናገደ ይገኛል
ቦይንግ ኩባንያ የማክስ 737 አውሮፕላን ምርት ሀላፊን ከሀላፊነት አነሳ፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ አቪዬሽን ኩባንያ የሆነው የአሜሪካው ቦይንግ የ737 ማክስ የተሰኙ አውሮፕላኖቹ ላይ ችግሮች ማጋጠማቸውን ተከትሎ ደንበኞቹን እና የገንዘብ ኪሳራዎችን በማስተናገድ ላይ ነው፡፡
የአሜሪካ ፌደራል ባለስልጣንም ቦይንግ ኩባንያ ማክስ 737 አውሮፕላኖችን እንዳያመርት ከአንድ ወር በፊት ጊዙያዊ እገዳ መጣሉ አይዘነጋም፡፡
ባለስልጣኑ በቦይንግ ላይ የጣለው ጊዜያዊ እገዳ ንብረትነቱ የአላስካ እና ዩናይትድ አየር መንገዶች የሆኑ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ መስኮቱ መገንጠሉን ተከትሎ እንደሆነ ኤፒ ዘግቧል።
ኩባንያው ባጋጠሙት የአውሮፕላን ምርቶች ምክንያት የማክስ 737 አውሮፕላን ምርት ክፍል ሀላፊ ኢድ ክላርክን ከሀላፊነት ማንሳቱን አስታውቋል፡፡
ኢድ ክላርክ ቦይንግ በዓለም አቀፍ ደረጃ 171 ማክስ 737 አውሮፕላኖች ከበረራ እንዲታገዱ ምክንያት ሆኗል በሚል ከሀላፊነት እንዳነሳቸው ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ 67 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ተስማማ
ቦይንግን ላለፉት 18 ዓመታት ያገለገሉት ኬቲ ሪንጎልድ ኢድ ክላርክን ተክተው የማክስ 737 አውሮፕላን ምርት ክፍል ሀላፊ ሆነው ተሸመዋልም ተብሏል፡፡
ቦይንግ ኩባንያ ከሶስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዢያ አየር መንገዶች ላይ አደጋ ካጋጠመ በኋላ ሁሉንም ማክስ አውሮፕላኖች በመላው ዓለም እንዳይበሩ እገዳ ጥሎ ነበር።
በአውሮፕላኖቹ ላይ በተሰራ የደህንነት ማሻሻያ ስራዎች ማክስ አውሮፕላኖች ዳግም ወደ በረራ ተመልሰዋል።
በቦይንግ አውሮፕላኖች ላይ አደጋ ማጋጠሙን ተከትሎ የኩባንያው አክስዮን ዋጋ በግማሽ እንዲቀንስ አድርጎትም ነበር።
ይህን ተከትሎ ለዓመታት በአቪዬሽን ትርፍ ቀዳሚ የነበረው ቦይንግ ኩባንያ ባለፉት አምስት ዓመታት በተቀናቃኙ ኤርባስ እንዲበለጥ አድርጎታል።