በጤና እክል ምክንያት ከኃላፊነት መልቀቃቸውን የቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አስታወቁ
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ትናንት የትምህርት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል
የተሰናባቹ ሚኒስትር በምን ኃላፊነት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እስካሁን አልታወቀም
የቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) በጤና እክል ምክንያት ከኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡
ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) “በጤንነቴ አሳሳቢነት የሙሉ ዕረፍት ጥያቄዬም ተቀባይነት በማግኘቱ ደስ ብሎኛል” ሲሉ በይፋዊ የማህበረሰብ ትስስር ገጾቻቸው ባሰፈሩት መልዕክት
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሰጧቸው እድል አመስግነዋል፡፡
“በቀጣይ ሀገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል”- ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
“እስካሁን በካቢኔዎ እንዳገለግል ዕድል ስለሰጡኝ አመሰግናለሁ” ሲሉም ነው የቀድሞው ሚኒስትር ያጻፉት፡፡
“በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ጊዜ ሚንስትር ዴኤታ በ2008 እና ሚንስትር 2009 በመሆኔ አሻራዎ አለበት፤ አሁንም በጤንነት ችግር ሙሉ የማረፍ ጥያቄዬን ስለተቀበሉ በጣም አመሰግናለሁ” ሲሉም አስቀምጠዋል፡፡
“ይህን ታላቅ ህዝብ ማገልገል ትልቅ ክብር ነው፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ እና የትምህርት ሚንስትር ሆኜ ለ 5 አመታት ህዝቤንና ሀገሬን አገልግያለሁ። በጤንነቴ አሳሳቢነት የሙሉ ዕረፍት ጥያቄዬም ተቀባይነት በማግኘቱ ደስ ብሎኛል”ም ነው ኢ/ር ጌታሁን ያሉት፡፡
የተሰናባቹ ሚኒስትር ቀጣይ ማረፊያ የት ለሆን እና በምን ኃላፊነት ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እስካሁን አልታወቀም፡፡ በእርሳቸውም ሆነ በመንግስትም በኩል ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተገለጸ ነገርም የለም፡፡
ኢ/ር ጌታሁን ባሰለፍነው ሰኞ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም የተካሄደውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሢመት ለመታደም ወደ አዲስ አበባ የመጡ እንግዶችን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው ሲቀበሉ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የኢትዮጵያ መንግስት ካቢኔ አባል ሆኑ
ትናንት አዳዲስ አባላት የተካተቱበት የሚኒስትሮች ካቢኔን ያዋቀሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አንጋፋውን ፖለቲከኛ እና ኢኮኖሚስት ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)ን የትምህርት ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል፡፡
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ መሆናቸውም ይታወቃል፡፡