ከቀረቡት 22 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል አምስቱ በአዲስ መልክ የሚዋቀሩ ናቸው
ዛሬ በመንግስት አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባርን ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ የመከረ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁን አጸደቀ፡፡
ምክር ቤቱ አስፈጻሚው አካል 22 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ኖረውት እንዲዋቀር የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ ነው ያጸደቀው፡፡
በጸደቀው ረቂቅ አዋጅ መሰረት በአስፈጻሚው አካል ከቀረቡት 22 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል አምስቱ በአዲስ መልክ የሚዋቀሩ ናቸው፡፡
በቅርቡ ሁሉን አካታች የሆነ ብሄራዊ የምክክር መድረክ ማካሄድ እንደሚጀመር ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ
እነዚህም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር እንዲሁም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሚሉ ናቸው፡፡
ኢንዱስትሪ ከንግድ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ከባህል፣ መስኖ ከውሃና ኢነርጂ እንዲሁም ባህል ከቱሪዝም ስፖርት ደግሞ ከወጣቶች ተነጥለው ራሳቸውን ችለው በሚኒስቴር ደረጃ እንዲዋቀሩ ተደርጓል፡፡
በኮሚሽን ደረጃ የነበሩት የስራ እድል ፈጠራ እና ፕላንም በተመሳሳይ መልኩ ራሳቸውን እንዲችሉና ሚኒስቴር እንዲሆኑ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ጸድቋል፡፡
በጸደቀው አዋጅ መሰረት ንግድ ሚኒስቴር ቀጣናዊ ጉዳዮችን ጭምር እንዲያካትትና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ትራንስፖርት የሎጂስቲክ ጉዳዮች ተጨምረውበት የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር እንዲባሉ ሆኗል፡፡
የህጻናትንና ወጣቶችን ጉዳይ ይከታተል የነበረው ሴቶች እና ህጻናት ሴቶችን ብቻ ይዞ ከቀድሞው ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እንዲዳበልና፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚል በአዲስ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡
“በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ከማንም ጋር ምንም አይነት ድርድር አይኖርም”- ፕሬዝዳንት ሣሕለ ወርቅ
የቀድሞው ከተማ ልማት፤ መሰረተ ልማትን እንዲያካትት ተደርጎ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በሚል ተቋቁሟል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተብሎ ሲያገለግል የነበረው ተቋም ቀድሞ ስያሜው እንዲመለስና በፍትህ ሚኒስቴርነት እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡
ግብርና ሚኒስቴር፣ የማዕድን ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሰላም ሚኒስቴር በስያሜያቸው እንዲቀጥሉ ሆኗል፡፡