ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በፊት ከግድቡ ውሃ እየለቀቀች ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ
ኢትዮጵያ የዓባይ ውሃን እያለማች ያለችው ለራሷፍላጎት እንጂ የታችኛው የተፋሰሱ ሀገራትን ለመጉዳት እንዳልሆነም ገልጸዋል
ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በፊት ከግድቡ ውሃ እየለቀቀች ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ
ኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በፊት ከግድቡ ሙሃ እየለቀቀች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስርት ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት መረጃ የሕዳሴ ግድብ አምና ከያዘው ውሃ ላይ አዲስ በተጠናቀቀው የውሃ ማስተንፈሻ በኩል ውሃ እየተለቀቀ መሆኑንና ኢትዮጵያም መረጃም እያጋራች ስለመሆኑ አስታውቀዋል።
የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትም ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚኖርበት “በሐምሌ ወይም ነሃሴ ወር ላይ ይካሄዳል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ይህም “በሱዳን ሊከሰት የሚችል የጎርፍ አደጋን የመከላከል ጥቅም ይኖረዋል” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ “ኢትዮጵያ የዓባይ ውሃን እያለማች ያለችው ለራሷፍላጎት ነው፤ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ለመጉዳት ሀሳብ የላትም” ብለዋል።
ባለፈው ዓመት የነበረው ከፍተኛ የዝናብ መጠን መጀመሪያው ዙር የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በስኬት እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን እና በጎረቤት ሀገር ሱዳን ላይ ይደረስ የነበረን የከፋ የጎርፍ አደጋ መከላከል ማስቻሉንም አስታውሰዋል።
የውሃ ማስተንፈስ ርምጃው በመጀመሪያው ሙሌት የተያዘውን የውሃ ከፍታ ዝቅ በማድረግ በግድቡ መካከል ሳይገነባ የቀረው የግድቡ አካል እንዲገነባ (በኮንክሪት እንዲሞላ) የሚያስችል ነው፡፡