አትሌት ሺዞ ካናኩሪ እ.አ.አ በ1912 በስዊድን ስቶኮልም የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ነው ጃፓንን በመወከል የተሳተፈፈው
የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰን ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያዊው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ እጅ የነበረ ሲሆን፤ አትሌቱም 42 ኪሎ ሜትር ከ 195 ሜትር ርቀቱን በሁለት ሰዓት ከሶስት ደቂቃ ከ 59 ማይክሮ ሰከንድ መግባቱ ይታወሳል፡፡ክብረ ወሰኑ አጁን በኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኢልዩድ ኪፕቾጌ እጅ ሲሆን አትሌቱም ርቀቱን ለመጨረስ ሁለት ሰዓት ከአንድ ሰከንድ ከ39 ማክሮ ሰከንድ ፈጅቶበታል።
በኪፕቾጌ በሁለት ሰከንድ ብቻ በመበለጥ የዓለም ቁጥር ሁለቱ የማራቶን ሯጭ ደግሞ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ነው።በጥቅሉ ማራቶንን ለማጠናቀቁ ከሁለት ሰዓት በላይ ቢፈጅም አንድ ጃፓናዊ አትሌት ግን ማረቶንን ለመጨረስ 54 ዓመታት በላይ መፍጀቱ ሁሉም አነጋጋሪ ሆኗል።
እ.አ.አ በ1912 በስዊድን መዲና ስቶኮልም ተካሂዶ በነበረው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ጃፓንን በመወከል ለመሳተፍ ሺዞ ካናኩሪ የተባለው አትሌት ምርጥ ሰዓት አስመዝግቦ ወደ ስፍራው ተጉዞ ነበር። አትሌት ሺዞ ካናኩሪ በዛን ዘመን በተካሄደው የማራቶን ውድድር የገባው በከፍተኛ የድካም ስሜት ከመሆኑም በላይ ይመገብ የነበረው ምግብ ሳይስማማው ቀርቶ እንደነበር ታሪክ ይገልጻል።
ውድድሩ በተደረገበት ዕለት በስቶክሆልም ከፍተኛ ሙቀት በመኖሩ በርካታ አትሌቶች ውድድሩን ማቋረጡ ይነገራል፡፡ ውድድሩን ካቋረጡት ውስጥ ጃፓናዊው አትሌት ሺዞ ካናኩሪ አንዱ ነበር። ካናኩሪ ውድድሩን አቋርጦ የጃፓን የስፖርት ባለስልጣናትን ሳያናግር ወደ ሀገሩ መመለሱን የአትሌቱ ታሪክ ይገልጻል።
እ.አ. አ በ1912 ከተደረገው የስቶክሆልም ኦሊምፒክ በኋላ የስዊድን ባለስጣናት አትሌቱ ጃፓን መኖሩን ሳያውቁ ጠፍቷል የሚል ግንዛቤ ነበራቸው። ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ እ.አ.አ በ1967 ከስዊድን ቴሌቪዥን ጋር በመነጋገር በ1912 የጀመረውን ውድድር እንዲያልቅ አደረገ።
ሺዞ ካናኩሪ ውድድሩን ለመጨረስ 54 ዓመታት፤ ስምንት ወራት፤ ስድስት ቀናት፤ አምስት ሰዓታት፤ 32 ሰከንድ እና 20 ነጥብ ሶስት ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶበታል፡፡
ውድድሩን የጨረሰውም ጋብቻ ፈጽሞ፤ ስድስት ልጆችና 10 የልጅ ልጆችን ካፈራ በኋላ መሆኑ ደግሞ አነጋጋሪ ሆናል፡፡ ምንም እንኳን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት ቢቋረጥም፤ ሺዞ ካናኩሪ በ1916 የክረምት ኦሊምፒክ ላይ ጃፓንን እንዲወክል ተመርጦ ነበር፡፡
ካናኩሪ በቤልጀም 1920 ላይ ማራቶንን ሁለት ሰዓት ከ 48 ደቂቃ ከ45 ነጥብ 4 ሰከንድ በማጠናቀቅ 16ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቆ ነበር።
በ1924 ደግሞ በድጋሚ ውድድር ላይ የተሳተፈው ካናኩሪ ማራቶንን ሳይጨርስ ቀርቶ ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ 1912 በስቶክሆልም ከተማ የጀመረውን የማራቶን ውድድር ከ54 ዓመታት በኋላ በእርጅና ዘመኑ በመጨረሱ ሁሌም ኦሊምፒክ በተቃረበ ቁጥጥር አነጋጋሪ ነው።
አትሌቱ ሺዞ ካናኩሪ እ.አ.አ በ1983 በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውም ነው የተነገረው።