
የባህር ዳር ከተማ የአዉሮፕላን ማረፊያውን ስያሜ ለመቀየር አራት ስሞችን በአማራጭነት አቅርቧል
የባህር ዳር አዉሮፕላን ማረፊያ ስያሜ ሊቀየር ነው
በባህ ርዳር ከተማ የሚገኘዉ የአዉሮፕላን ማረፊያ ስያሜ መቀየር አስፈላጊ መሆኑን የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ማስታወቁን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ፡፡
የአዉሮፕላን ማረፊያዉ ከዚህ በፊት “በላይ ዘለቀ“ እና “ግንቦት 20“ የተሰኙ ስያሜዎች የነበሩት ቢሆንም በዚህ ስዓት ስያሜዉን መቀየር አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት ነው የባህር ዳር ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ያሰፈረው፡፡
በመሆኑም የአዉሮፕላን ማረፊያዉን ስያሜ ለመቀየር የህዝብ አስተያየት መቀበል የግድ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥበት ለማስቻል የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ እንደ መነሻ አቅርቧል፡፡
በዚህም መሰረት ቢሮዉ ያቀረባቸዉ ስያሜዎች ባህር ዳር ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ፣ በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ፣ ዓባይ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ እና ጣና ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ናቸው፡፡
በዚህም መሰረት ስያሜዎች እንደ መነሻ በመቀመጣቸው ሕብረተሰቡ የተሻለ የሚለውን እንዲመርጥ ጥሪ ቀርቧል፡፡