የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደቡብ አፍሪካ አቻው ሊሰጥ የሚችለው አውሮፕላኖችን እና ሌሎች ሙያዊ ድጋፎችን እንደሆነ አስታወቀ
ደቡብ አፍሪካ አየር መንገዱን ከገባበት የብድር አዘቅት ለማውጣት 10 ቢሊዬን ዶላር እንደሚያስፈልግ ማስታወቋ የሚታወስ ነው
አየር መንገዱ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር በሽርክና ለመስራት በመነጋገር ላይ ይገኛል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደቡብ አፍሪካ አቻው ሊሰጥ የሚችለው አውሮፕላኖችን እና ሌሎች ሙያዊ ድጋፎችን ብቻ እንደሆነ አስታወቀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ሊሻረክ የሚችለው አውሮፕላን ከመስጠት በተጨማሪ ሙያዊ ድጋፎችን በማድረግ እንደሆነ አስታወቀ፡፡
አየር መንገዱ በዕዳ እና ተያያዥ የአስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ሊተባበር እንደማይችል አስታውቋል፡፡
አሰራሮችን ለማዘመንና ለማሻሻል ድጋፎችን እያደረጉ እንደሆነ ያስታወቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም “በእዳ ክፍያ ወይም የሰው ኃይልን ለመቀነስ በሚደረገው ወጪ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት የለንም” ብለዋል ብሉምበርግ በአዲስ አበባ የሰጡት ባለው ቃለ ምልልስ ገለጻ፡፡
“እዳን፣የሰው ኃይልን በመሳሰሉ የቆዩ ጉዳዮች ላይ ለመስራት አንፈልግም፤ ምክንያቱም በገንዘብ ጉዳይ ብቻም ሳይሆን የተቋሙን እንደገና መደራጀት መምራት በራሱ ለእኛ በጣም ከባድ ነው”ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚው፡፡
አውሮፕላኖችን በመስጠት፣ ፓይለቶችን ፣ ቴክኒሻኖችን ፣ አመራሮችን በመስጠት ሌሎች ሙያዊ ድጋፎችን በማድረግ አየር መንገዱን በቀላሉ ለማስጀመር እንደሚፈልጉም ገልጸዋል፡፡
አየር መንገዱ ካሉት አውሮፕላኖች በተሻለ የዘመኑ የኤርባስ እና የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመስጠት እንደሚችሉም ነው አቶ ተወልደ የተናገሩት፡፡
የደቡብ አፍሪካ መንግስት አየር መንገዱን ከገባበት የብድር አዘቅት ለማውጣት 10 ቢሊዬን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡
ገንዘቡ የበረራ ቲኬቶችን ተመላሽ ለማድረግ እና ከስራ ለመቀነስ ለተስማማሙ 4 ሺ ገደማ ሰራተኞች ደሞዝና የስራ መፈለጊያ ለመስጠት የሚውል ነው፡፡
በዚህም ምክንያት አየር መንገዱን ከገባበት ችግር ለማውጣት የሚያስችል አቅም እንዳላቸው እና በሽርክና ለመስራት እንደሚችሉ ከገለጹ የተለያዩ የግል ባለሃብቶች እና ተቋማት ጋር ምክክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ከነዚህ መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንዱ ነው፡፡