ዝነኛው ኢትዮጵያዊ ተወዛዋዥ በታዋቂው ‘ቴድ ቶክ’ ላይ የ4 ደቂቃዎች ንግግር ሊያደርግ ነው
መላኩ 5 አህጉራትንና 14 ሃገራትን ካካለለው ምርጫ አንዱ ሆኖ የተመረጠው በድንቅ ተወዛዋዥነቱ ነው
መላኩ በላይ የ‘ቴድ ቶክ’ የዘንድሮ ‘ፌሎው’ 20 ሰዎች መካከል አንዱ ነው
የታዋቂው ‘ቴድ ቶክ’ የዘንድሮ ‘ፌሎው’ ሆነው ከተመረጡ 20 ሰዎች መካከል አንዱ ዝነኛው ኢትዮጵያዊ ተወዛዋዥ እና የዳንስ ኬሪዮግራፈር መላኩ በላይ ነው፡፡ መላኩ 5 አህጉራትንና 14 ሃገራትን ካካለለው ምርጫ አንዱ ሆኖ የተመረጠው በድንቅ ተወዛዋዥነቱና በኢትዮጵያ ባህል አምባሳደርነቱ ነው፡፡
‘ፌሎው’ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢትዮጵያ መመረጡንም ፕሮግራሙን የተመለከቱ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
የፈንድቃ ባህል ማዕከል መስራች እና ባለቤቱ መላኩ በቀጣዩ ወር ሚያዚያ የመጀመሪያ ሳምንት (APRIL 10 – 14 ) በካናዳ ቫንኩቨር በሚዘጋጅ ዓለም አቀፍ መርሐ ግብር ላይ ንግግር የሚያደርግም ይሆናል፡፡
የባህል አምባሳደሩ መላኩ እንዴትና ምን ሰርቶ እንደተመረጠ፣ በመመረጡ ስለተሰማው ነገር እና የሚያደርገውን ንግግር በተመለከተ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጓል፡፡
ቻናሉ ላይ ይመዝገቡ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረ ገጻችንን ይጎብኙ
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ትዊተር: https://twitter.com/AlAinAmharic
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsam...
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic