በሰሜናዊ ናይጀሪያ የምትገኘው ግዛት ገዥ ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ የሚቻለውን እንደሚያደርጉ ለተማሪዎቹ ቤተሰቦች ገልጸዋል
የናይጀሪያ ባለስልጣናት በናይጀሪያ ሰሜንምእራብ በምትገኘው ዛምፋራ ግዛት 317 ተማሪዎች በታጣቂዎች ከታፈኑ በኋላ በግዛቷ የሚገኙ ሁሉም አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ወስነዋል፡፡
የዛምፋራ ገዥ የሆኑት ቤሎ ማታዎሌ የመዝጋት እርምጃው የተወሰደው ተማሪዎች ከጥቃት ለመከላከል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የናይጀሪያ ፖሊስ ባለፈው አርብ ከሴቶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 317 ተማሪቆች መታገታቸውን አረጋግጧል፡፡ ማታዎሌ ተጠቂዎቹ ቤተሰቦች እንደተናገሩት መንግስት ተማሪዎች ለማስለቀቅ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
ድርጊቱ ከፈረንጆቹ ከታህሳስ ወር ወዲህ በአፍሪካ ቁጥር አንድ የህዝብ ቁጥር ባላት ሀገር በገፍ የተፈጸመ ሦስተኛው እገታ ነው ተብሏል፡፡ ለእገታው ሃላፊት የወሰዳ አካል የለም የተባለ ሲሆን በአካባው ግን ይህን ሊፈጽሙ የሚችሉበ ሽፍቶች በቦታው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል፡፡
የአሁኑ እገታ የተፈጸመው በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ በተመሳሳይ በትምህርት ቤት በተፈጸመ ጥቃት 27 ተማሪዎችን ጨምሮ 40 ሰዎች ታግተው ከተወሰዱ በቅርብ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
ባለፈው ታህሳስ ወር ደግሞ በሰሜንምዕራብ ናይጄሪያ ካጺና ግዛት ከሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት 300 ወንድ ተማሪዎች የታገቱ ሲሆን ለዚህም ቦኮ ሀራም ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡ ይሔው ጽንፈኛ ታጣቂ ቡድን በፈረንጆቹ 2014፣ 270 የቺቦክ ሴት ተማሪዎችን በማገት መነጋገሪያ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ያኔ ከታገቱት ተማሪዎች 100 የሚሆኑት እስካሁን ያሉበት አይታወቅም፡፡