ዩ.ኤ.ኢ በፀጥታው ም/ቤት ተለዋጭ አባል መሆን በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል
ሀገሪቱ መመረጧ ዓለም አቀፉ ማበረሰብ በሀገሪቱ ፖሊሲ ላይ ያለውን እምነት ያሳየበት ነው
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በፀጥታው ም/ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ተመረጠች
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለሁለት ዓመታት በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ ማገኘቷ ሰፊ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገለጸ።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲሁም የዓረቡ ዓለም ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የደስታ መግለጫን የላኩ ሲሆን፤ ዩ.ኤ.ኢ መቀመጫውን ማግኘቷም ዓለም አቀፉ ማበረሰብ በሀገሪቱ ፖሊሲ ላይ ያለውን እምነት ያሳየበት እንዲሁም የዲፕሎማሲያዊ ስርዓቷ ቅልጣፋነት እና ውጤታማነት ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በተባበሩት መንግስታ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ገሪንፊልድ፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ በማሸነፏ የመልካም ምኞት ምልእክት አስተላልፈዋል።
በተመድ የሳዑዲ አረቢያ ተወካይ አምባሳደር አበደላህ ቢን ያህያ አል ማውሊሚም እና በተመድ የኢራቅ ተወካይ ለዩ.ኤ.ኢ የመልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አህመድ ናስር አል ሞሃመድ አል ህመድ አል ጅብሪል አል ጃቢር አል ሙባረክ አል ሳባህ ዩ.ኤ.ኢ በተመድ የፀጥታው ም / ቤት መቀመጫ ማገኘቷ ደስታ መግለጫ አስተላፈዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዩኤኢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ዓለም አቀፍ ትብብር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድ አል ናሕያን ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታም ዩ.ኤ.ኢ በምክር ቤቱ የአባልነት ቆይታዋ ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን በማስጠበቅ ረገድ ሀላፊነቷን በምትወጣበት ጊዜ ኩዌት አስፈላጊውን እገዛ እንደምታደርግ አስታውቀዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለሁለት ዓመታት በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ እንዲኖራት በዛሬው እለት መመረጧ ይታወቃል፡፡
“የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም ዩኤኢን ለ 2022-2023 የፀጥታው ም/ቤት ከአምስት አባላት አንዷ እንድትሆን ነው የመረጣት።