መኪናው በፀሃያማ የአየር ሁኔታ በቀን እስከ 740 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል
የኔዘርላንድስ ኤንድሆቨን ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፀሃይ ኃይል የሚሰራ ሚኪና ሰርተው ከሰሞኑ ይፋ አድርገውታል።
የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች የሰሩት ሰማያዊ እና ነጭ ቀለም ያለው መኪናው ወደ ቤትነት ተቀይሮ እንደ መኖሪያ የሚያገለግል መሆኑም ተነግሯል።
በፀሃያማ የአየር ሁኔታ ውስጥ በቀን እስከ 740 ኪሎ ሜትር መጓዝ ይችላል የተባለው መኪናው፤ የከሚናው ባትሪ ከጸሃይ በሚያገኘው ኃይል በተሸከርካረው ውስጥ የሚገኙ ማቀዝቀዣ፣ የቡና ማፍያ እና ላፕቶፕ ለማስጠቀም ያስችላል።
የ23 ዓመቷ የባዮ ሜዲካል እንጂነሪንግ ተማሪ ቫን ዳስለር፤ “የፀሃይ ብርሃን በማይኖርነት ሰዓት ትንሽ ልንቸገር እንችላልን፤ ነገር ግን ከኤሌክትሪክ ኃይል ማገኘት እንዲችል በዲዛይናችን ውስጥ አካተናል” ብላለች።
መኪናው በባዶ መንገድ ላይ በሰዓት እስከ 12 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችልም ተናገራለች።
ሌላው በመኪናው ስራ ላይ የተሰማራው የ21 ዓመቱ ተማሪ ተጂን ተር፤ “በፀሃይ ኃይል የሚሰራው መኪና ልክ እንደ ሌሎች መኪናዎች የፍሬን እና ሌሎች ፔዳሎች አሉት” ብሏል።
መኪናው ለመንገድ ተስማሚ መሆኑን ለመሞከርም ከኔዘርላንድስ ወደ ስፔን ለአንድ ወር የሚቆይ ጉዞ ባሳለፍነው አርብ መጀመሩም ተነግሯል።
የመኪናው ስራ ውስጥ የተሰማሩ የፈጠራ ባለሙያዎች ቡድን፤ አዲስ የሰሩት መኪና ፖለቲከኞች እና የመኪና አምራቾች ወደ አረንጓጌ ኢነርጂ ለመሸጋገር የሚያገርጉትን ሽግግር ለማፋጠን ይረዳል ብለዋል።