በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሄዝቦላ መሪ የተገደለበትን ቦታ ጎበኙ
ነስረላህ ሄዝቦላን ለ 30 አመታት በመምራት በመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ ጠንካራ ኃይል እንዲሆን አድርጎታል
በእስራኤል እና ሄዝቦላ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈው መስከረም ወር የሄዝቦላ መሪ ነስረላህ የተገደለበት ቦታ ለጋዜጠኞች እና ለህዝብ ክፍት እንዲሆን በር ከፍቷል
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የቀድሞ የሄዝቦላ መሪ ሀሰን ናስረላህ በእስራኤል የአየር ጥቃት የተገደለበትን ቦታ ቡድኑ እንዲጎበኝ ከፈቀደ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጎብኝተዋል።
በቤይሩት በተፈጸመው የአየር ጥቃት የተፈጠረው ጉድጓዳ ቦታ በቀይ መብራት እና በሄዝቦሃ ባንዲራ ደምቆ አምሽቷል። በቦታው የተሰበሰቡ ህጻናት፣ ሴቶች እና ወንዶች "ለአገልግሎትህ፣ ነስረላህ" በማለት በሄዝቦላ ደጋፊዎች የሚዘወተረውን አስለቃሽ መፈክር አሰምተዋል።
ነስረላህ ሄዝቦላን ለ 30 አመታት በመምራት በመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ ጠንካራ ኃይል እንዲሆን አድርጎታል።
ባለፈው ረቡዕ እለት በአሜሪካ አደራዳሪነት በእስራኤል እና ሄዝቦላ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈው መስከረም ወር የሄዝቦላ መሪ ነስረላህ የተገደለበት በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ የሚገኘው ቦታ ለጋዜጠኞች እና ለህዝብ ክፍት እንዲሆን በር ከፍቷል። ነስረላህ የተገደለበት በደቡባዊ ቤሩት ዳርቻ የሚገኘው ደሂህ የተባለው ቦታ ቀደም ሲል ለህዝብ ዝግ የነበረ እና ከፍተኛ ጥበቃ ሲደረግበት የቆየ ነው።
የሄዝቦላ መሪን የገደለው የእስራኤል የአየር ጥቃት ከ80 በላይ አሜሪካ ሰራሽ በንከር ቦምቦችን የተጠቀመ ሲሆን የሄዝቦላ ማዕካላዊ መዘዣ ጣቢያ በሚገኝባት ሀሬክ ህሬክ መንደር ያሉ በርካታ ህንጻዎችንም አውድሟል።
ህዝብ ትናንት ምሽት ለመጀመሪያ ጊዜ በቦታው ሲሰበሰብ የወደመውን ቦታ እና በፍንዳታው የተፈጠረውን ጉድጓድ እየተዘዋወሩ ተመልክቷል።
ባለፈው መስከረም ወር የሄዝቦላ መገደል ዜና ሊባኖስን እና መላው አለምን አስደንግጦ ነበር። ነስረላህ ሄዝቦላ ከእስራኤል ጋር በ2006 ካደረገው ጦርነት ወዲህ አልፎ አልፎ በአደባባይ ብቅ የሚል እና ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለት ነበር።
ነስረላህ ከመስከረም ወር እስከ ተኩስ አቁም ስምምነቱ ድረስ በእስራኤል የአየር ጥቃት የተገደለ ከፍተኛ የሄዝቦላ መሪ ነው።
የነስረላህ ግድያ፣ የሄዝቦሃ አጋር የሆነችውን ኢራንን እና እስራኤልን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ቀጥተኛ ግጭት እንዲገቡ ምክንያት ሆኗል።