ሶስት የትምባሆ ድርጅቶች በሰዎች ላይ ላደረሱት ጉዳት 23 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማሙ
ድርጅቶቹ ምርታቸው የሰዎችን ጤና እንደሚጎዳ የሚያስረዳ መልዕክት ለተጠቃሚዎች አላሳወቁም ተብሏል
ሲጋራውን ያጨሱ ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው የጉዳት ካሳ እንደሚከፈላቸው ተገልጿል
ሶስት የትምባሆ ድርጅቶች በሰዎች ላይ ላደረሱት ጉዳት 23 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማሙ፡፡
ፊሊፕ ሞሪስ፣ ብሪቲሽ አሜሪካ እና ጃፓን ቶባኮ ድርጅቶች ለዓመታት የትምባሆ ምርቶቻቸውን በማምረት እና ለዓለም ገበያ በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡
እነዚህ ድርጅቶች በካናዳዊያን ሲጋራ አጫሽ ዜጎች ላይ ላደረሱት ጉዳት ካሳ እንዲከፍሉ ክስ ተመስርቶባቸው ነበር፡፡
ድርጅቶቹ ክሱ የተመሰረተባቸው የትምባሆ ምርቶቻቸውን በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት አላሳወቁም በሚል ነው፡፡
ተጠቃሚዎችም ሲጋራ የሳምባ እና ሌሎች መተንፈሻ አካላት ላይ በሚያስከትለው ጉዳት ሰዎች ለካንሰር ህመም መጋለጣቸው ተገልጿል፡፡
የካሳ ይገባናል ክርክሩ ከ10 ዓመት በፊት በካናዳዋ ኩቤክ ፍርድ ቤት ተጀምሮ የነበረ ሲሆን ከዓመታት በኋላ ኩባያዎቹ ጉዳዩን በስምምነት ለመጨረስ እንደተስማሙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ሶቱ ኩባንያዎች 23 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለተጎጂዎች ለመክፈል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
የድርጅቶቹን ትምባሆ ምርቶች ተጠቅመው ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች የካሳ ክፍያው ለህጋዊ ወራሾቻቸው እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
ኩባንያዎቹ ለመክፈል የተስማሙትን 23 ነትብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ እያንዳንዳቸው ምን ያህል መክፈል እንዳለባቸው ተስማምተው እንደሚመጡም ተናግረዋል ተብሏል፡፡