ቲክቶክ ደንበኞቹን ረጅም ቪዲዮ እንዲሰሩ ግፊት እያደረገ ነው ተባለ
ቲክቶክ በዓለም ተመራጭ እና ተወዳጅ እንዲሆን ይዞት የመጣው የአጭር ቪዲዮ ነበር
ኩባንያው ረዘም ያሉ ቪዲዮዎችን ለሚሰሩ ሰዎች የተሻለ ክፍያ እንደሚከፍልም አስታውቋል
ቲክቶክ ደንበኞቹን ረጅም ቪዲዮ እንዲሰሩ ግፊት እያደረገ ነው ተባለ፡፡
ከሶስት ዓመት በፊት አጫጭር ቪዲዮዎችን በማቅረብ የማህበራዊ ትስስር ኢንዱስትሪን የተቀላቀለው ቲክቶክ በአጭር ጊዜ በመላው ዓለም ተወዳጅ ሊሆን ችሏል፡፡
የቲክቶክን ተወዳጅነት በማየትም ዩቲዩብ፣ፌስቡክ እናኢንስታግራም ተጠቃሚዎች አጫጨር ቪዲዮዎችን ማሰራጨት እንዲችሉ ሊፈቅዱ ችለዋል፡፡
በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ቲክቶክ አሁን ደግሞ ደንበኞቹን ረዘም ያሉ ቪዲዮዎችን እንዲሰሩ ግፊት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ኩባንያው እንደገለጸው ከቲክቶክ ክፍያ ለማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች አንድ ደቂቃ እና ከዛ በላይ ርዝመት ያላቸውን ቪዲዮዎች መስራት ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡
ኩባንያው ይህን የሚያደርገው ከኢንዱስሪው የሚያገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንደሆነ ያስታወቀ ሲሆን ረጅም ጊዜ በመተግበሪያው ላይ ለሚቆዩ ደንበኞችም የተለየ ጥቅም እንደሚሰጥም ገልጿል፡፡
የኢለን መስኩ ኤክስ የድምጽ እና ቪዲዮ ጥሪ አገልግሎት ሙከራ ጀመረ
ይሁንና አጫጭር ቪዲዮዎችን በመስራት ብዙ ተከታይ ያፈሩ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች በቲክቶክ አዲስ ውሳኔ ምቾት እንዳልተሰማቸው ተናግረዋል፡፡
ቲክቶክ ታዋቂነትን እና ብዙ ተጠቃሚዎችን ማግኘት ያቻለው አጫጭር ቪዲዮዎችን በማግኘታቸው የነበረ ሲሆን አሁን ወደ ረጅም ቪዲዮ መመለሱ ደንበኞቹን እንዲያጣ ሊያደርገው እንደሚችልም ተሰግቷል፡፡
ኩባንያው ስራ ሲጀምር አንድ ደቂቃ እና ከዛ በላይ ቪዲዮዎችን በመልቀቅ የነበረ ቢሆንም ቀስ በቀስ ወደ ሶት ደቂቃ አሁን ደግሞ የ15 ደቂቃ ሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በአዲሱ የቲክቶክ ህግ መሰረት 10 ሺህ እና ከዛ በላይ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች በታየላቸው መጠን ክፍያ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡