በተፎካካሪዎች ጠንካራ ጫና እየደረሰበት ያለው ትዊተር በአለም የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ መቀጠል ይፈልጋል
የትዊተር ኩባንያ ተጠቃሚዎች የድምጽ እና የቪዲዮ ጥሪ ለማድረግ የሚያስችላቸውን አገልግሎት እየሞከረ መሆኑን አስታውቋል።
ይህ የአገልግሎት ማሸሻያ ሰዎች ከጋደኞቻቸው ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት ይጨምራል ተብሏል።
እየለማ ያለው ይህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች 'በዳይሬክት ሜሴጅ አፕ ላይ ኮሎ አይከን' የሚለውን በመጫን የድምጽ ወይም የቨዲዮ ጥሪ ለማድረግ ያስችላቸዋል።
ትዊተር ይህን አገልግሎት ወደ ተግባር ሲያስገባ፣ በትዊተር ላይ ሰዎች የነበራቸውን አጠቃቀም መቀየር ጨምሮ በርካታ ችግሮች እንደሚገጥሙት ተገልጿል።
ትዊተር ይህን አገልግሎት ይፋ ያደረገው፣ የትዊተር ባለቤት ኢለን መስክ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ባደረገው ለውጥ መሰረት ነው ተብሏል።
በተፎካካሪዎች ጠንካራ ጫና እየደረሰበት ያለው ትዊተር በአለም የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ መቀጠል ይፈልጋል።
በቅርቡ የኢንስታግራም እና ፌስቡክ እናት ኩባንያ የሆነው የማርክ ዛከርበርጉ ሜታ ከቲዊተር ጋር ተቀራራቢ አገልግሎት የሚሰጥ ትሪድስ የተሰኘ ማህበራዊ ሚዲያ አድርጓል።
ከኢንስታግራም ገጽ ጋር የተሳሰረው ትሪድስ እስከትናንት ድረስ 30 ሚሊዮን ደንበኞች ማፍራቱን ሜታ ገልጿል።
የሜታው ትሪድስ መቋቋም በትዊተር ዘንድ አልተወደደም።
ትዊተር፣ ሜታ የትዊተርን ሚስጢር የሚያዉቁ የቀድሞ ሰራተኞችን ቀጥሯል ሲል ከሷል። ትዊተር የእምሮአዊ የፈጠራ መብቱን ለማስከበር እንደሚንቀሳቀስም በጠበቃው በኩል አስታውቋል።