የኢለን መስኩ ኤክስ የድምጽ እና ቪዲዮ ጥሪ አገልግሎት ሙከራ ጀመረ
ኩባንያው የቻይናው ዊ ቻት የትስስር ገጽ የሚሰጠውን አገልግሎት ሁሉ የማቅረብ ውጥን እንዳለው ተገልጿል
በቀጣይም ከመደዋወል ባለፈ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት መስጠት እጀምራለሁም ብሏል
የኢለን መስኩ ኤክስ የድምጽ እና ቪዲዮ ጥሪ አገልግሎት ሙከራ ጀመረ፡፡
በቀድሞ ስሙ ትዊትር የተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጽ በፈረንጆቹ 2022 ሚያዚያ ወር ላይ ነበር በኢለን መስክ የተገዛው፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሖኑት ኢለን መስክ በቀድሞው ስሙ ትዊትር የተሰኘውን የትስስር ገጽ በ44 ቢሊዮን ዶላር ከገዙት በኋላ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ስያሜውን ወደ ኤክስ የቀየሩት መስክ ሰራተኞችን መቀነስ፣ የማረጋገጫ ምልክትን በወርሃዊ ክፍያ ማድረግ፣ አካውንት ለመክፈት አንድ ዶላር ክፍያ መጠየቅ፣ ለልዩ ደንበኞች መረጃዎችን በክፍያ መድረግ እና ሌሎችንም ማሻሻያዎችንም አድርገዋል፡፡
አሁን ደግሞ ኤክስ ኩባንያ የድምጽ እና ቪዲዮ ኮል ወይም የመደዋወያ አገልግሎትን ለመስጠት በሙከራ ላይ መሆኑን የድርጅቱ ባለቤት ኢለን መስክ በዚሁ ትስስር ገጻቸው ላይ ተረናግረዋል፡፡
ባለጸጋው ኤክስን ልክ እንደ ቻይናው ዊ ቻት የትስስር ገጽ የጹሁፍ፣ ደምጽ፣ ቪዲያ ኮል እና ሌሎችንም የተሟሉ አገልግሎቶችን የማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡
የትዊተር ተጠቃሚዎችን እያስኮበለለ ያለው “ማስቶዶን” መተግበሪያ
በቀጣይም ኤክስ የትስስር ገጽ የገንዘብ ማስተላለፍ አገልግሎት መስጠት የማስጀመር እቅድ እንዳላቸውም ኢለን መስክ ገልጸዋል፡፡
ደንበኞች አገልግሎቱን ለማግኘት እንደሌሎች የትስስር ገጾች ስልክ ቁጥርን እንደግዴታ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም የተባለ ሲሆን ቀስ በቀስ አዳዲስ አገልግሎቶችን እንደሚጀምርም ተገልጿል፡፡
ኢለን መስክ ኩባንያውን ከገዙ በኋላ የተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር የ11 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ ወደ 225 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ ሲገለጽ የድርጅቱ ሰራተኞች በገፍ መልቀቅ እና በነጻ የሚቀርቡ አገልግሎቶች እየቀነሰ መሄድ ለደንበኞች መቀነስ እንደምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡