በረመዳን ፆም ወቅት ድርቀትን ለመቀነስ የሚረዱን ጠቃሚ ነጥቦች ምንድናቸው?
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ ተደርጎ የሚወሰደው የረመዳን ፆም ከተጀመረ አንድ ሳምንት ሆኖታል
አማኞች ለረጅም ሰአታት ምግብ ስለማይመገቡ እና ፈሳሽ ስለማይወስዱ ድርቀት ወይም ኮንስቲፔሽን ሊያጋጥም ይችላል
በረመዳን ፆም ወቅት ድርቀትን ለመቀነስ የሚረዱን 10 ጠቃሚ ነጥቦች ምንድናቸው?
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ ተደርጎ የሚወሰደው የረመዳን ፆም ከተጀመረ አንድ ሳምንት ሆኖታል።
አማኞች ለረጅም ሰአታት ምግብ ስለማይመገቡ እና ፈሳሽ ስለማይወስዱ ድርቀት ወይም ኮንስቲፔሽን ሊያጋጥም ይችላል።በፆም ወቅት ሊያጋጥም የሚችል ድርቀትን ለመቀነስ መደረግ የሚገባቸው በርካታ ዘዴዎች እንዳሉ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ድርቀትን ለመቀነስ ከሚረዱን ተግባራት ውስጥ ቀዳሚ የሚባሉት የሚከሉት ናቸው።
-በፋይበር የበለጸገ አረንጓዴ ሳላድ መመገብ
-ለስላሳ መጠጦችን አለመጠጣት ወይም በጣፋጭ መጠጦች ላይ ስኳር አለመጨመር
-እንደ ታምሪንድ እና ቆማር አል አዲን የመሳሰሉ ድርቀትን የሚያስወግዱ መጠጦችን መጠቀም
-በስኳር የበለጸጉ ጣፋጭ መጠጦችን ማስወገድ
-በቁርስ ሰአት በቂ ውሃ መጠጣት
-የምግብ እንሽርሽሪት የሚያውኩ ደረቅ ምግቦችን እና ከረሜላን አለመጠቀም
-በሰሁር ወቅት እርጎ መጠጣት
-ለምግብ እንሽርሽሪት ሂደት የሚጠቅሙ በፋይበር የበለጸጉ ፍራፍሬዎችን በየቀኑ መመገብ
-ቅመም ያለባቸው ምግቦችን አለመመገብ
-እንደ ሻይ ያሉ ካፊን የበዛባቸውን መጠጦች አለመጠቀም