በረመዳን ፆም የመጀመሪያ ሳምንት ወቅት ራስምታትን ለማስወገድ የሚረዱ 6 ነጥቦች
የእስልምና እምነት ተከታዮች የጤና ሁኔታን ከግምት ሳያስገቡ ለረጅም ሰአታት ይፆማሉ።
የሚፆሙ ሰዎች በተለይም በመጀመሪያ ሳምንት ላይ የራስምታት ህመም ያጋጥማቸዋል
በረመዳን ፆም የመጀመሪያ ሳምንት ወቅት ራስምታትን ለማስወገድ የሚረዱ 6 ነጥቦች
የእስልምና እምነት ተከታዮች የጤና ሁኔታን ከግምት ሳያስገቡ ለረጅም ሰአታት ይፆማሉ።
በረመዳን ኢፍጣር የሚዘጋጁ የተለያዩ ምግቦች እና መጠጦች በእነዚህ ረጅም ሰአታት ውስጥ የሚኖረውን የጥማት ሰሜትን በእጥፍ ከፍ እንዲል ያደርጉታል።
ስለዚህ እያንዳንዱ የሚፆም ሰው የአመጋገብ ሁኔታውን ማሻሻል እና በፆም ወቅት ጥንካሬ ሊሰጡ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ እንዳለበት ባለሙያዎች ይመክራሉ።
የሚፆሙ ሰዎች በተለይም በመጀመሪያ ሳምንት ላይ የራስ ምታት በሽታ ያጋጥማቸዋል። ይህ በካፊን መጠን መቀነስ፣ በከፍተኛ የደም ግፊት ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል።
በካይሮ በሚገኘው የናሽናል ኢንስቲቲዩት ኦፍ ኑትሪሽን ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ሰአድ ሀማድ የራስ ምታት በትክክል አለመመገብን ጨምሮ በበርካታ ምክንያቶች ይከሰታል።
ዶክተር ሀማድ ለአል ዐይን ኒውስ እንደተናገሩት በመጀመሪያ የረመዳን ፆም ሳምንት የራስምታት የሚከሰተው ከፍተኛ የካፊን መጠን ያላቸውን ምግቦች እና መጠጦችን መጠቀም ስለምናቆም ነው ይላሉ።
የረመዳን ወር ከመቅረቡ በፊት ቀስበቀስ የምንወስደውን የመጠጥ መጠን መቀነስ እና የምንጠጣበትን የጊዜ ልዩነት ማስፋት መፍትሄ እንደሚሆን ዶክተር ሀማድ ተናግረዋል።
የኑትሪሽን ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት በፆም ወቅት ማጨስን ለረጅም ሰአት ማቆም በተለይ በመጀመሪያዎቹ የረመዳን ቀናት ራስምታት እንዲከሰት ያደርጋል።
"በርግጥ ሲጋራ ማጤስን ማቆም ያለብን በረመዳን ወቅት ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ነው፤ ነገርግን የሚፆም ሰው ከረመዳን ቀደም ብሎ መጠኑን መቀነስ መጀመር አለበት" ይላሉ ዶክተሩ።
ዶክተር ሀማድ በረመዳን ወቅት ራስምታት እንዳያመን ማድረግ ያለብንን ነጥቦች ጠቁመውናል።