የ2024 የኦሎምፒክ አስተናጋጇ የፈረንሳይዋ ፓሪስ የኦሎምፒክ ሰንደቅ አላማውን ከቶኪዮ እጅ ተረክባለች
ላለፉት 2 ሳምንታት ሲካሄድ የነበረው የ32ኛው የ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ በትናትናው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተፅእኖ ስር ሆኖ በደማቅ ስነ ስርዓት የተጀመወረው ኦሎምፒኩ በተለያዩ ደማቅ ስነ ስርዓቶችም ነው የተዘጋው
በመዝጊያው ስነ ስርዓት ላይም ለ2024 የኦሎምፒክ አስተናጋጇ የፈረንሳይዋ ፓሪስ የኦሎምፒክ ሰንደቅ አላማውን ከቶኪዮ እጅ ተረክባለች።
በዘንድሮ የቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ከ205 ሀገራት የተውጣቱ ከ11 ሺህ በላይ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ 93 ሀገራም የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ችለዋል።