94 ነጥብ 5 በመቶ ተሽከርካሪዎች በ10 ሀገራት የተመረቱ ናቸው
የአለም ንግድ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በ2022 ከ85 ሚሊየን በላይ ተሽከርካሪዎች ተመርተዋል።
ከተመረቱት ተሽከርካሪዎች ውስጥ 46 ከመቶው በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የተመረቱ ናቸው፤ ሀገራቱ 699 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን ሽጠዋል።
አሜሪካ በ2022 138 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከአውሮፓ ህብረት ቀጥሎ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች።
ጃፓን፣ ሜክሲኮ እና ቻይና በርካታ ተሽከርካሪዎችን ለአለም ገበያ በማቅረብ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
10ሩ ዋና ዋና ተሽከርካሪ አምራች ሀገራት 94 ነጥብ 5 ከመቶ የአለም የተሽከርካሪ ንግድን ተቆጣጥረዋል።