የጃፓኑ ኩባንያ ባለፈው አመት በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሽያጭ ካስመዘገቡ የተሽከርካሪ ሞዴሎች አራቱን በስሙ አስመዝግቧል
የጃፓን መኪና አምራች ኩባንያ ቶዮታ በ2022 10 ነጥብ 5 ሚሊየን ተሽከርካሪዎችን ሸጧል።
ይህም ቶዮታን ለሶስት ተከታታይ አመታት የአለማችን ቀዳሚው የመኪና ሻጭ ኩባንያ አድርጎታል።
የጀርመኑ ቮልስዋገን ኩባንያ በ8 ነጥብ 6 ሚሊየን ተከታዩን ደረጃ ይዟል።
በ2022 በብዛት ከተሸጡ 10 የተሽከርካሪ ሞዴሎች ውስጥ አራቱ በጃፓኑ ቶዮታ የተመረቱ መሆናቸውንም የሬውተርስ ዘገባ ያሳያል።
ባለፈው አመት 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ተሽከርካሪዎችን የሸጠው ፎርድም በኤፍ ሲሪየስ ሞዴል መኪናው ከፍተኛ ሽያጭ ማስመዝገብ ችሏል።
በ2022 ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገቡ የተሸከርካሪ ሞዴሎችን ይመልከቱ፦