ጦራቸውን በርካታ ታንክ ያስታጠቁ ሀገራት
ብሪታንያ በመጀመሪያው የአለም ጦርነት ያስተዋወቀችው ታንክ ከ100 አመት በኋላም በአውደ ውጊያዎች ጉልህ ሚናው አልቀዘቀዘም
አንዳንዶች ግን የዩክሬኑ ጦርነት የታንክ ዘመን እንዳበቃለት ማሳያ ነው ይላሉ
ብሪታንያ የጦር ታንክን በፈረንጆቹ 1915 ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀች ሀገር ናት።
“ሊትል ዋሊ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ታንክ በአንደኛው የአለም ጦርነት እንግሊዝና ፈረንሳይ የጀርመንን ጦር ሲገጥሙ ጥቅም ላይ ቢውልም የሚፈለገውን ውጤት አላስገኘም።
ጀርመኖች ከዚህ ጦርነት ተምረው “ስቱርምፓንዜርዋገን” የሚል መጠሪያ የሰጡትን ታንክ በ1918 ሰርተዋል።
ገና ሲያዩት በጠላይ ላይ ሽብር የሚለቀው፥ ከፍተኛ የተኩስ አቅም እና ጋራ ሸንተረሩን እየደረማመሰ ለማለፍ የማይቸገረው ታንክ በሁለቱም የአለም ጦርነቶች የውጊያ አውድን በመቀየር ይነሳል።
የአሜሪካው “ኤም1 አብራምስ”፣ የሩሲያ “ቲ-14 አርማታ”፣ የጀርመኑ “ሊዮፓርድ 2” በአለም ኣአቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካላቸው ታንኮች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።
የድሮን ቴክኖሎጂ ታንኮችን ይበልጥ የጥቃት ኢላማ ውስጥ እንዲገቡ ቢያደርጋቸውም አሁንም ድረስ ተፈላጊ ናቸው።
በዩክሬኑ ጦርነት ከ2 ሺህ 800 በላይ ታንኮች የወደሙባት ሩሲያ፥ ፋብሪካዎቿ በብዛት ታንክ እንዲያመርቱ ከማድረግ ባሻገር ጥቃትን ቀድመው የሚለዩ ሴንሰሮች እንዲገጠሙላቸው እያደረገች ነው።
ቻይናም የግዛቴ አካል ናት የምትላትን ታይዋን ወደ እናት ምድሯ ለማዋሃድ ከአየር እና ባህር ሃይሏ ባሻገር የምድር ጦሯ በጠንካራ ታንኮች እንዲጠናከር ካዘዘች ሰነባብታለች።
በርካቶች የዩክሬኑ ጦርነት የታንኮች ዘመን ማብቃቱን ያመላከተ ነው ቢሉም የዘርፉ ተንታኞች ግን በቴክኖሎጂ እየዘመነ ይቀጥላል እንጂ ከጦርነት አውድማ እንደማይወጣ በርግጠኝነት ይናገራሉ።