ቲ-14 አርማታ ታንክ ያለ ሰው የሚንቀሳቀሰ እና በርቀት ካለ ካፕሱል በመቆጣጠር መተኮስ የሚችል ሲሆን በሰአት 80 ኪሎ ሜትር መሄድ የሚችል ነው
ሩሲያ ቲ-14 አርማታ የተሰኘውን ታንክ በዩክሬን ጦርነት ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ እያዋለች መሆኑ ተገልጿል።
የዩክሬን ይዞታዎችን ለመምታት ጥቅም ላይ የዋለው ይህ ታንክ በቀጥታ የማጥቃት ዘመቻ ላይ ግን እየተሳተፈ አለመሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ታንኩ በክንፉ ላይ ተጨማሪ መከላከያ የተገጠመለት ነው።
ቲ-14 አርማታ ታንክ ያለ ሰው የሚንቀሳቀሰ እና በርቀት ካለ ካፕሱል በመቆጣጠር መተኮስ የሚችል ሲሆን በሰአት 80 ኪሎ ሜትር መሄድ የሚችል ነው።
ባለፈው ጥር፣ ታንኩ ጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለም በሚል ምክንያት በዩክሬን ያሉ የሩሲያ ኃይሎች ታንኩን ለመቀበል ቸልተኝነት ሲያሳዩ እንደነበር የእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ገልጾ ነበር።
ቲ-14 ታንኮችን መላክ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ውሳኔ ነው ሲልም ድርጅቱ መግለጹ ይታወሳል።
ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2015 ብቅ ያደረገችው ይህ ታንክ በብዛት እንዲመረት ማዘዟ ተዘግቧል።
ሩሲያ ኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋቱን እና ይህም ለደህንነቷ እንደሚያሰጋት በመግለጽ ነበር ከ14 ወራት በፊት በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተችው።