አስከሬኖችን በህገ ወጥ መንገድ ለዩንቨርሲቲዎች የሚሸጡት ሰራተኞች
ሆስፒታሉ አንድን አስከሬን በ1 ሺህ 200 ዶላር እየሸጠ ነበር ተብሏል
በስፔን ቫሌንሲያ የሆስፒታል ሰራተኞች አስከሬኖችን ለምርምር ስራዎች ይሸጡ እንደነበር ፖሊስ አረጋግጧል
አስከሬኖችን በህገ ወጥ መንገድ ለዩንቨርሲቲዎች የሚሸጡት ሰራተኞች
በስፔን ቫሌንሲያ ውስጥ ያለ ሆስፒታል ሰራተኞች አስከሬኖችን እንደሚሸጡ የሀገሪቱ ፖሊስ በምርመራ ማረጋገጡ ተገልጿል፡፡
እንደ ፖሊስ ምርመራ ከሆነ የሆስፒታሉ አስከሬን ክፍል ሰራተኞች ለዩንቨርሲቲዎች ምርምር አንድን አስከሬን በ1 ሺህ 200 ዶላር ሲሸጡ ቆይተዋል፡፡
ሰራተኞቹ ለህክምና ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎችን አስከሬኖቹን የሚሸጡት ሰዎቹ ከመሞታቸው በፊት የሰውነታቸውን አካላት ለሳይንሳዊ ምርምሮች እንዲውሉ ፈቅደዋል የሚል የተሳሳተ ማስረጃ በማዘጋጀት እንደሆነ የፖሊስን የምርመራ ዋቢ አድርገው የዘገቡ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
ሰራተኞቹ ላለፉት አንድ ዓመት ይህን ሲያደርጉ ነበር የተባለ ሲሆን በተለይም ስደተኞች፣ እንግዶች እና ጠያቂ ቤተሰብ የሌላቸውን ሰዎች አስከሬን በብዛት ለሽያጭ እንደሚያውሏቸውም ተገልጿል፡፡
ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች የሰውነታቸው ክፍላቸውን በፈቃደኝነት ለዩንቨርሲቲዎች ለምርምር የሚሰጡ ሰዎች ቢኖሩም ሟቹ ቃል ከገባው ተቋም ውጪ የተሸለ ገንዘብ ለሚከፍሉ ዩንቨርሲቲዎች የተሰጡ አስከሬኖች እንዳሉም በምርመራው ተገኝቷል፡፡
የደቡብ አፍሪካው ፓስተር አስከሬን "ትንሳኤ" ሲጠበቅ 579 ቀናትን ሳይቀበር መቆየቱ ተነገረ
ዩንቨርሲቲዎች በአስከሬኖቹ ላይ ተገቢውን ምርምር ካደረጉ በኋላ በመመለስ ስርዓተ ቀብራቸው እንዲፈጸም እና ወጪውንም ራሳቸው እንዲችሉ የሀገሪቱ ህግ የሚያስገድድ ቢሆንም ዩንቨርሲቲዎቹ ክፍያውን ቢፈጽሙም ተገቢው ስርዓተ ቀብር አልተፈጸመላቸውም ተብሏል፡፡
በዚህ ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ የሆስፒታሉ የአስከሬን ክፍል ሰራተኞች እና ሃላፊ በቁጥጥር ስር ውለው ክስ እንደተመሰረተባቸው ተገልጿል፡፡