የሕንዷ ቤንጋሉሩ እና የአረብ ኢምሬቷ ሻርጃህ ቀጣዮቹ የባለጸጋዎች መኖሪያ ዋና ማዕከል ይሆናሉም ተብሏል
የብሪክስ አባል ሀገራት ምን ያህል ቢሊየነሮች አላቸው?
አሁን ላይ 10 አባል ሀገራት ያለው ብሪክስ 4 ሺህ 716 ሚሊየነሮች እና 549 ቢሊየነሮች ያሉት ሲሆን የባለጸጋዎች ቁጥር በፍጥነት ከሚያድግባቸው ሀገራት መካከል ዋነኛው ጥምረት ይሆናል ተብሏል፡፡
ዠዓለም አቀፉ የጥናት ተቋም ሀንሌይ እና ፓርትነርስ የብሪክስ ሀገራት በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ የሚኖራቸውን ኢኮኖሚ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ ተቋም ትንበያ መሰረት አሁን ላይ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች አንድ ሚሊዮን ዶላር እና ከዛ በላይ ሀብት ያላቸው ሲሆን ይህ አሀዝ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በ85 በመቶ ያድጋል ተብሏል፡፡
ይህም አንድ ሚሊዮን ዶላር እና ከዛ በላይ ሀብት ያላቸው ዜጎች ቁጥር አሁን ካለበት 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ወደ 3 ሚሊዮን ገደማ ከፍ ይላል፡፡
እስከ 2034 ድረስ ባሉት 10 ዓመታት ውስጥ ሀብታም ከሚሆኑ 10 ከተሞች ውስጥ አምስቱ በቻይና ይገኛሉ የተባሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ዱባይ፣ አቡዳቢ፣ ሞምባይ፣ ዴልሂ እና ሞስኮ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ አባል ሀገራት ሽልማት አሸነፈ
የህንዷ የቴክኖሎጂ ማዕከል ቤንጋሉሩ ከብሪክስ ሀገራት ውስጥ ፈጣን እድገት የምታስመዘግብ ከተማ ትሆናለች የተባለ ሲሆን የአረብ ኢምሬቷ ሻርጃህ ሚሊየነሮችን በመሳብ ቀዳሚ እንደምትሆን ተገልጿል፡፡
የሳውዲዎቹ ሪያድ እና ጅዳህ ከተሞች በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ያላቸው ሚሊየነር ብዛት በ100 እጥፍ ይጨምራልም ተብሏል፡፡
የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታወን ከተማ አሁን ላይ ያላት ሚሊየነሮች ብዛት 7 ሺህ 400 ሲሆን ከ10 ዓመት በኋላ ይህ ቁጥር ወደ 13 ሺህ 500 እንደሚጨምር ተገልጿል፡፡