ከተመሰረቱ አጭር እድሜ ያላቸው ሀገራት የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ደቡብ ሱዳን፣ ሞንቴኔግሮ እና ሰርቢያ በቅርቡ የሀገርነት እውቅና ከተሰጣቸው ሀገራት መካከል ናቸው
ጀርመን እና የመን ተነጣጥለው የነበሩ አካባቢዎችን ዳግም ውህደት በመፍጠር ድጋሚ የሀገርነት እውቅና ካገኙት መካከል ተጠቃሽ ናቸው
ከተመሰረቱ አጭር እድሜ ያላቸው ሀገራት የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
እንደ ዓለም አቀፉ ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው መረጃ ከሆነ ጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን የዓለማችን ወጣቷ ሀገር ስትባል በፈረንጆቹ 2011 ላይ ነበር በሱዳን እውቅና መሰረት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሀገርነት እውቅና የተሰጣት፡፡
የቀድሞዎቹ ዩጎዝላቪያ ስር የነበሩት ሰርቢያ፣ ሞንቴኔግሮም በፈረንጆቹ ሚሊኒየም እና 2006 ላይ የሀገርነት እውቅና ሲሰጣቸው የቀድሞዎቹ ቼኮዝሎቫኪያ በመባል የሚታወቂት ቼክ ሪፐብሊክ እና ስሎቫኪያም በ1993 ለየብቻቸው ሀገር ተብለው ተዋቅረው እውቅናም አግኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የቀድሞ ግዛት አንድ አካል የነበረችው ኤርትራም በህዝበ ውሳኔ እንደ ሀገር እውቅና ከተሰጣት 31ኛ ዓመቷን አክብራለች፡፡
አሁን ጀርመን ተብላ የምትጠራው ሀገር ከዚህ በፊት ምስራቅ እና ምዕራብ ጀርመን በሚል የተለያዩ ሀገራት የነበሩ ሲሆን በ1990 ላይ ውህደት ፈጽመው ሀገር ተብለዋ፡፡
እንዲሁም የአሁኗ የመን ይህን ስያሜዋን ከመያዟ በፊት የመን አረብ ሪፐብሊክ እና ደቡባዊ የመን የሚል በሚል ስያሜ ሁለት ሀገር የነበሩ ሲሆን በ1990 ላይ ውህደት በመፈጸም የአሁኑን አንድ የመን ስያሜ ልትይዝ ችላለች፡፡