ከፍተኛ የዩራኒየም ክምችት ያላቸው ሀገራት (በቶን)
ዩራኒየም ለአቶሚክ ቦምብ እና ለኒዩክሌር የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫዎች በግብአትነት የሚውል ማዕድን ነው
ከአለማችን የዩራኒየም ሃብት ግማሹ በአውስትራሊያ፣ ካዛኪስታን እና ካናዳ ይገኛል
ሩሲያ እና የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) የገቡበት ፍጥጫ አለማችን ለሶስተኛው የአለም ጦርነት መቃረቧን እንደሚያሳይ ይነገራል።
ሶስተኛው የአለም ጦርነት “የኒዩክሌር ጦርነት” እንደሚሆንም ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በተደጋጋሚ ሲያነሱ ይደመጣል።
ከኢራን እስከ ሰሜን ኮሪያ፥ ከአሜሪካ እስከ ሩሲያ ለአለም ስጋት የሆኑ የኒዩክሌር ጦር መሳሪያዎች የሚሰሩት ከዩራኒየም ነው።
አሜሪካ በፈረንጆቹ 1945 የጃፓን ከተሞችን (ሄሮሽማ እና ናካሳኪ) የጣለችዉ አቶሚክ ቦምብ ከኮንጎ በተገኘ ዩራኒየም መሰራቱን መረጃዎች ያሳያሉ።
ዩራኒየም ከኒዩክሌር ጦር መሳሪያዎችና ማብለያዎች ጋር በተያያዘ ስሙ አስፈሪ ቢሆንም ለኒዩክሌር ሃይል ማመንጫዎች፣ በኒዩክሌር ለሚሰሩ መርከቦችና ሌሎች መሳሪያዎች ዋነኛ ግብአት ነው።
የዚህ ተፈላጊ ማዕድን ክምችት በኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ፉክክር ውስጥ ባሉት ሀገራት አነስተኛ ነው የሚለው ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው፥ ከአለማችን የዩራኒየም ሃብት ግማሹ በአውስትራሊያ፣ ካዛኪስታን እና ካናዳ እንደሚገኝ ይገልጻል።
ሩሲያ በዩራኒየም ክምችት አምስተኛ ደረጃን ስትይዝ፥ አሜሪካ በ112 ሺህ ቶን 15ኛ ደረጃን ይዛለች።
የኒዩክሌር ሃይል ማመንጫ ያላቸውና የኒዩክሌር ጦር መሳሪያዎችን በስፋት የሚያመርቱ ሀገራት ዩራኒየም ከሌሎች ሀገራት በመግዛት ክፍተታቸውን ይሞላሉ።
ከፍተኛ የዩራኒየም ክምችት ያላቸው 10 ሀገራት ዝርዝርን ይመልከቱ፦