በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የገነኑ አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው?
ናይጀሪያዊው ቪክተር ኦስሜን በጆርጅ ዊሀ የተያዘውን የግብ አግቢነት ሪከርድ ሰብሯል
የአሁኑ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሀ ኦስሜን ባሎንዶርን የማሸነፍ እድል አለው ሲል አሞካሽቶታል
የአውሮፓ እግር ኳስ በሚከተላቸው መርሆች ፈታኝ እና የተለየ ችሎታ የሚጠይቅ ውድድሮች አሉበት።
በዚህ ምክንያት ፈታኝ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ለአፍሪካዊያን ተጫዋቾች በቀላሉ የሚለመድ እንዳልሆነ ይገለጻል።
እነዚህን እና ሌሎች ፈተናዎችን ተቋቁመው በችሎታቸው ተመልካቾችን ቁጭ ብድግ የሚያደርጉ አፍሪካዊያን በየጊዜው አንጸባርቀዋል።
ከአውሮፓ ተወዳጅ ከሆኑት የእግር ኳስ ውድድሮች መካከል የእግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሲሆን የሚከተሏቸው የጥራት ማስጠበቂያ መርሆች እና የጨዋታ ስነ ምግባሮች በዓለማችን ተወዳጁ ሊግ ሆኗል።
በዚህ ውድድር በበዛበት ሊግ ውስጥ አፍሪካዊያን ተጫዋቾች መካከል ግብጻዊው መሀመድ ሳላህ በሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነትን ክብረ ወሰን ሰብሯል።
የሊቨርፑል እግር ኳስ ክለብ የሚጫወተው መሀመድ ሳላህ በሊጉ ያስቆጠረውን ጎል ወደ 120 በማሳደግ የምንግዜም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አፍሪካዊ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች ሆኗል።
ሌላኛው አፍሪካዊ ተጫዋች ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ 111 ጎል በማስቆጠር ሁለተኛ ሲሆን ኮትዲቯራዊው የቀድሞው የቸልሲ ተጫዋች ዲድየር ድሮግባ በ104 ጎል ሶስተኛው አፍሪካዊ ተጫዋች ተብሏል።
ከፈረንሳይ ሊግ አንድ ደግሞ ካሜሩናዊው ማማዱ ኒይንግ ለማርሴይ 100 ጎል በማስቆጠር ቀዳሚው አፍሪካዊ ተጫዋች ነው።
ኮንጎዋዊ ሻባኒ ኒንዳ ለሬንስ እና ሞናኮ እግር ኳስ ክለቦች 88 ጎሎችን በማስቆጠር በፈረንሳይ ከተጫወቱ አፍርካዊያን መካከል ሁለተኛው ታሪካዊ ተጫዋች ነው።
ላይቤሪያዊው ጆርጅ ዊሀ ለሞናኮ እና ፒኤስ ጂ በመጫወት 84 ጎሎችን በማስቆጠር ሶስተኛው ታሪካዊ ተጫዋት አስብሎታል።
በስፔን ላሊጋ ደግሞ ካሜሩናዊው አይረሴ ተጫዋች ሳሙኤል ኢቶ በ162 ጎሎች የምንግዜም ከፍተኛው እግር ኳስ ተጫዋች ተብሏል።
በሪያል ማድሪድ የተገፋው ኢቶ ወደ ባርሴሎና በማቅናት 280 ጨዋታዎችን በማድረግ ከባርሴሎና ጋር የላሊጋ፣ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ሌሎችንም ዋንጫዎችን አሸንፏል።
ማሊያዊ ፍሬዲ ካኑቴ ሲቪያ ክለብን ከተቀላቀለ በኋላ 89 ጎሎችን በማስቆጠር በላሊጋው ታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ጎል ያስቆጠረ አፍሪካዊ ተጫዋች ነው።
የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ናይጀሪያዊው ክርስቶፈር ኦህን ደግሞ 42 ጎሎችን በማስቆጠር ሶስተኛው አፍሪካዊ ተጫዋች ተብሏል።
ከጀርመን ደግሞ ጋቦናዊው ፔር ኢሜሪክ ኦቦምያንግ በ98 ጎሎች የመጀመሪያው ቀዳሚ ጎል አስቆጣሪ መሆኑን ጎል ስፖርት ዘግቧል።
በጣልያን ሴሪኤ ደግሞ በናፖሊ የነገሰው ናይጀሪያዊው ቪክተር ኦስሜን 47 ጎሎችን በማስቆጠር ታሪክ ጽፏል።
የኦስሜን አዲስ ሪከርድ መስበርን ተከትሎ የቀድሞው ኤሲ ሚላን እግር ኳስ ተጫዋች እና የአሁኑ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት የሆነው ጆርጅ ዊሀ 46 ጎሎችን በማስቆጠር በጣልያን ሁለተኛው አፍሪካዊ ተጫዋች ሆኗል።
ኬታ ባልዴ እና ጆርጊንሆ በእኩል በ41 ጎሎች በጣልያን ሶስተኛ ታሪካዊ አፍሪካዊ ተጫዋችነት ደረጃን ይዘዋል።
ናፖሊ የዘንድሮን የጣልያን ሴሪኤ ዋንጫ እንዲያነሳ ያደረገው ተጫዋች ኦስሜን ተጨማሪ ጎሎችን እንደሚያስቆጥር ይጠበቃል።
ላለፉት በርካታ ዓመታት በጣልያን ሴሪኤ ታሪክ አፍሪካዊ ከፍተኛ ጎል ሪከርድን ይዞ የነበረው ጆርጅ ዊሀ በቪክተር ኦስሜን መሻሻሉን ተከትሎ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት በትዊተር ገጹ ላይ ጽፏል።
ጆርጅ ዊሀ እንዳለውም ቪክተር ኦስሜን ገና ብዙ ሪከርዶችን እንደሚሰብር ገልጾ የባሎንዶር ውድድርን የማሸነፍ አቅም እንዳለው እና ጠንክሮ እንዲሰራም ምክረ ሀሳቡን አጋርቷል።