ስፖርት
በአለም ዋንጫው ሃትሪክ የሰሩ ተጫዋቾች ስንት እንደሆኑ ያውቃሉ?
ፓርቹጋላዊው ጎንሳሎ ራሞስ በኳታሩ የአለም ዋንጫ ስዊዘርላንድ ላይ ሶስት ጎሎችን አስቆጥሩ የቀደሙትን ከዋክብት ተቀላቅሏል
ገርድ ሙለር፣ ጋብሬል ባብቲስታ እና በርት ፓቴናውድን ጨምሮ በአለም ዋንጫው 48 ተጫዋቾች ሃትሪክ ሰርተዋል
በአለም ዋንጫው ከጅምሩ አንስቶ እስከ 2018 ድረስ ከ2500 በላይ ጎሎች ተቆጥረዋል።
48 ተጫዋቾችም በአንድ ጨዋታ ሶስት ጎሎች ማስቆጠር ችለዋል።
በኳታሩ የአለም ዋንጫ ፖርቹጋላዊው ጎንሳሎ ራሞስ ስዊዘርላንድ ላይ ሶስት ጎሎችን ሲያስቆጥር የአለም ዋንጫው 53ኛ ሃትሪክ ሆኖ ተመዝግቧል።
ፎቶ - ጎንሳሎ ራሞስ
የመጀመሪያው ሃትሪክ ኡራጓይ ባዘጋጀችው የ1930 (1ኛው) የአለም ዋንጫ ነው የተመዘገበው።
አሜሪካዊው በርት ፓቴናውድ ፓራጓይ ላይ ሶስት ጎሎችን አከታትሎ በማስቆጠር የአለም ዋንጫውን ሀትሪክ አሀዱ ብሏል።
በወቅቱ ፊፋ ፓቴናውድ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎልን ፊፋ በቡድን አጋሩ ቶም ፈሎሪ ስም በመመዝገቡ 35 አመታትን ከወሰደ ክርክር በኋላ ለፓቴናውድ ተወስኗል። ይሁን እንጂ ተጫዋቹ ይህን ውሳኔ ሳይሰማ ህይወቱ አልፏል።
ፎቶ - ገርድ ሙለር
ጀርመን ከኤድመንድ ኮነን (1934 ) እስከ ቶማስ ሙለር (2014) ሰባት ጊዜ ተጫዋቾቿ ሃትሪክ በመስራታቸው ቀዳሚዋ ናት።
ጀርመናዊው ገርድ ሙለር በአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ከአንድ ጊዜ በላይ ሃትሪክ ከሰሩ አራት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።
ሙለር በሶስት ቀናት ውስጥ ሀትሪክ በመድገምም ስሙን በታሪክ መዝገብ አስፍሯል።
ፎቶ - ጋብሬል ባብቲስታ
አርጀንቲናዊው ጋብሬል ባብቲስታም በሁለት ተከታታይ የአለም ዋንጫዎች ስድስት ጎሎችን በማስቆጠር የሚተካው አልተገኘም።
አርጀንቲና በአለም ዋንጫው ካስመዘገበችው የአራት ሀትሪክ ሁለቱ በባብቲስታ ተመዝግቧል።
ሀንጋሪም በአለም ዋንጫ ታሪክ አራት ሃትሪክ የሰሩ ተጫዋቾችን አስመዝግባለች።
በ1994 ኤልሳቫዶርን 10 ለ 1 ባሸነፉበት ግጥሚያ በ55ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ገብቶ በሰባት ደቂቃዎች ሃትሪክ የሰራው ላዝሎ ኪስ የሀንጋሪ ክስተት እንደነበር ይታወሳል። ኪስ ተቀይሮ ገብቶ ሃትሪክ በመስራትም ብቸኛው ተጫዋች ነው።
ጎቲያኖ ራሞስም ሮናልዶን ተክቶ በመግባት ሃትሪክ በመስራቱ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።