ሕንዶች የሚያመልኳት የዕምሮ ህመምተኛ ሴት
ቶፒ አማ በሚል ስያሜ የምትታወቀው ሕንዳዊት ህይወቷን በጎዳናዎች ላይ ያደረገች ሴት ብትሆንም ብዙዎች ያመልኳታል
ዝምተኛ ነች የተባለችው ይህች ሴት አልፎ አልፎ ትርጉም የማይሰጡ ቃላትን ስትናገር የሚያመልኳት ሰዎች ይደሰታሉ ተብሏል
ሕንዶች የሚያመልኳት የዕምሮ ህመምተኛ ሴት
የሕንዷ ትሩቫናማላይ ከተማ በታሚል ናዱ ክልል ስር የምትገኝ በጎብኚዎች የምትወደድ ከተማ ነች፡፡ ሶት ሚሊዮን ገደማ በሚኖርባት በዚች ታሪካዊ ከተማ ውስጥ የምትኖር አንድ ጎልማሳ ሴት አለች፡፡
ቶፒ አማ በሚል ስም የምትጠራው ይህች ሴት ኑሮዋ በድልድዮች ስር ያደረገች ቢሆንም በተወሰኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ግን እንደ አምላክ ትታያላች፡፡
ኮፍያ በማድረግ የምትታወቀው ይህች ሴት በብዛት ዝምታን የምታበዛ ሲሆን አልፎ አልፎ የጥንት ሂንዱ ቅላጼ ያላቸው ቃላቶችን ትናገራለች፡፡
ይህ የጥንት ሂንዱ ቋንቋ ቅላጼ ያላቸውን ቃላት መናገሩ ይህችን ሴት እንደ ማንኛውም ሰው አድርጎ መቀበል እንደከበዳቸው እና አምላክ እንደሆነች የሚያምኑባት ሰዎች እየጨመሩ መጥተዋል፡፡
ቶፒ አማ በጎዳናዎች ላይ ስትንቀሳቀስ ከኋላዋ ሆነው የሚከተሏት ሰዎች ብዙ ናቸው የተባለ ሲሆን ቀምሳ የምትተዋቸውን ምግቦች ተሻምተው የሚቀምሱ እና የሚከፋፈሉ ሰዎችም እየጨመረ ነውም ተብሏል፡፡
ወደ ጉዳያቸው የሚያልፉ ሰዎች ድንገት ቶፒ አማን በጎዳናዎች ላይ ስታልፍ ሲያዩ ጎንበስ ብለው እንደሚሰግዱላት እና የሆነ ቃላት እስክትናገርም አጎንብሰው እንደሚጠብቁ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በሕንድ ሚስቱ የማገጠችበት ባል የፈጸመው ድርጊት አነጋገረ
የተወሰኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ በተቃራኒው ቶፒ አማ አምላክ ሳትሆን የዐዕምሮ ህመምተኛ መሆኗን እና ህክምና እንደሚያስፈልጋት በመናገር ላይ ናቸው፡፡
በሕንድ ከአምልኮ ጋር በተያያዘ እንዲህ አይነት ነገር መመልከት የተለመደ ቢሆንም በቶፒ አማ ላይ የሚታየው ነገር ግን ስህተት ነው የተባለ ሲሆን አለባበሷን እና ድርጊቷን በማየት ብቻ ቶፒ አማ የአዕምሮ ህክምና እንድታገኝ ግፊት እያደረጉ ቢሆንም አምላካቸው እንደሆነች የሚያምኑት ግን ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው እያሉ ናቸው፡፡