በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ሁለት እጩዎች ቀርበው ነበር
ድሮፓዲ ሙርሙ 15ኛዋ የሕንድ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።
በሕንድ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድሮፓዲ ሙርሙ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ተመራጯ ፕሬዝዳንት በህንድ ታሪክ ከሀገሪቱ ነባር ጎሳዎች መካከል የመጀመሪያዋ ፖለቲከኛ ያደርጋቸዋል ተብሏል።
በምርጫው ላይ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ሆነው ተወዳደሩት ያሽዋት ሲንግ ከገዥው ፓርቲ እጩ ሆነው በቀረቡት ሙርሙ ተበልጠዋል።ተራመጯ ፕሬዝዳንት በሕንድ ታሪክ ሁለተኛዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነውም ተመርጠዋል ተብሏል።
ሕንድን ላለፉት ስድስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ራም ናት ኮቪንድ ስልጣናቸውን ከሁለት ቀናት በኋላ ለተመራጯ ፕሬዝዳንት ሙርሙ ያስረክባሉ።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ወደ ተመራጯ ፕሬዝዳንት ሙርሙ በኒው ዴልሂ ከተማ ባለው መኖሪያ ቤታቸው በማምራት እንኳን ደስ አለዎት ማለታቸውንም ዘገባው አክሏል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተመራጯ ፕሬዝዳንት ጉብኝታቸው በኋላም ሕንድ ያሉ ሲሆን ሕንድ ከነባር ጎሳዎቿ ፕሬዝዳንቷን በመምረጧ ትኮራለች ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
የተመራጯ ፕሬዝዳንት ሙርሙ ወደ ስልጣን መምጣት ሚሊዮን እንስት ሕንዳዊያንን ያበረታታል ሲሉም ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለዋል።