ጎብኝዎች 150 አመት እድሜ ያለውን ሀውልት በማፍረስ ተከሰሱ
ይህ ሀውልት 1.70 ሜትር ከፍታ አለው
በማህበራዊ ሚዲያ ፎቶ ለማጋራት ሰልፊ የተነሱ የጀርመን ቱርስቶች በሰሜን ጣሊያን ቪላ ውስጥ የሚገኝ ውድ ዋጋ ያለውን ሀውልት በማፍረስ ተከሰሱ
በማህበራዊ ሚዲያ ፎቶ ለማጋራት ሰልፊ የተነሱ የጀርመን ቱርስቶች በሰሜን ጣሊያን ቪላ ውስጥ የሚገኝ ውድ ዋጋ ያለውን ሀውልት በማፍረስ ተከሰሱ።
ከጎብኝዎቹ መካከል ሁለቱ በአርቲስት ኢንርኮ ቡቲ የተሰራውን በፍውንቴኑ ውስጥ ያለውን "ዶሚና" በማቀፍ እና ሌሎች ደግሞ በእንጨት በመግፋት እንዲገነደስ አድርገዋል ተብሏል።
ይህ ሀውልት 1.70 ሜትር ከፍታ አለው።
የቪላው ስራ አስኪያጅ ጎልፈርኒ በ17ቱም የጀርመን ቱሪስቶች ላይ ለፖሊስ ቅሬታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።
ጎብኝዎቹ ጣሊያንን የለቀቁ ሲሆን ይህ ድርጊታቸው የታወቀው ቪላው ውስጥ በነበረው የደህንነት ካሜራ ነው።
ሀውልቱ 150 አመት አካባቢ እድሜ ያለው እና 218 ሺ ዶላር ዋጋ እንደሚገመት የገለጹት ስራአስኪያጁ ጎልፈርኒ በፋውንቴኑ ላይ የደረሰው ተጨማሪ ጉዳት ለመጠገን አስቸጋሪ እንደሚሆን ተናግረዋል።
የጎብኝዎቹ ተግባር እንዳሳዘናቸውም ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
ቀደም ሲል የእንግሊዝ ጎብኝዎች በሀውልቱ ላይ ጹሁፍ ሲጽፉ መታየታቸው ጥያቄ በጣሊያናውያን ዘንድ ቁጣ ፈጥሮ ነበር።