ፔንታጎን ጾታቸውን የቀየሩ የአሜሪካ ጦር አባል ወታደሮችን ሊያሰናብት መሆኑ ተገለጸ
ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮች በ60 ቀናት ውስጥ ሰራ መልቀቅ መጀመር እንዳለባቸው የፔንታጎን ማስታወሻ ያመለክታል

ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ 15 ሺህ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ መግለጻቸው ይታወሳል
ጾታቸውን የቀየሩ የአሜሪካ ጦር አባል ወታደሮችን ከስራ እንደሚያሰናብት የአሜሪካ መከላከያ ሚኒቴር ቢሮ (ፔንታጎን) አስታወቀ።
ከአንድ ወር በፊት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ስልጣን የያዙት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ የሚያግድ ፕሬዝዳታዊ ትእዛዝ መፈረማቸው ይታወሳል።
ይህንን ትእዛዝ ወደ ማስፈጸም የገባው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒቴር ቢሮ (ፔንታገን) ትናት ለፍርድ ቤት በላከው ማስታወሻ፤ ልዩ ፈቃድ እስካላገኙ እና ነጻ እስካልሆኑ ድረስ ጾታቸውን የቀየሩ የአሜሪካ ወታደሮች ከሰራዊቱ እንደሚለያዩ አስውቋል።
ፔንታገን እየወሰደ ያለው እርምጃ ጾታውን የቀየሩ አሜሪካውያን በውትድርናን እንዳይቀላቀሉ ወይም በውትድርና እንዳያገለግሉ ማገድ ነው የጠባለ ሲሆን፤ ይህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ካሳለፉት ውሳኔ በላይ ከበድ ያለ እንደሆነም ተነግሯል።
ፔንታገን በዚህ ወር ከአሁን በኋላ ጾቸውን የቀየሩ ግለሰቦች የአሜሪካን ጦር እንዲቀላቀሉ እንደማይፈቅድ እና አገልግሎት ላይ ላሉ አባላት ከሥርዓተ-ፆታ ለውጥ ጋር የተያያዙ ሂደቶችን ማከናወን ወይም ማመቻቸት እንደሚያቆም ተናግሯል።
ፔንታገን ትናንት ምሽት ለፍርድ ቤት በላከው ማስታወሻ ክልከላውን የጾታ ለውጥ አድርገው በአሙሪካ ጦር ውስጥ እያገለገሉ ባሉ ወታሮች ላይም ተፈጻሚ እንደሚሆን አስታውቋል።
ፔንጎን በማስታወሻ በ30 ቀናት ውስጥ ጾቸውን የቀየሩ የጦር አባላትን የመለየት ሂደት እንደሚያከናውን እና በቀጣይ 30 ቀናት ደግሞ ከአሜሪካ ጦር የማባረር ሂደት እንደሚጀምር አታውቋል።
በጥቅሉ ጾታቸውን የቀየሩ የአሜሪካ ጦር አባል ወታደሮች በ60 ቀናት ውስጥ ሰራ መልቀቅ መጀመር እንዳለባቸው የፔንታጎን ማስታወሻ ያመለክታል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን በያዙ የመጀመሪያ ቀናት ጾታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ የሚያግድ ፕሬዝዳታዊ ትእዛዝ መፈረማቸው ይታወሳል።
ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው የሚያምኑት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንዲታገዱ ነው ያዘዙት።
በዶናልድ ትራምፕ ውሳኔ መሰረት 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮች ከስራቸው ሊባረሩ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዶኔልድ ትራምፕ በከ2016-2020 ድረስ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ዓመታት ውስጥ ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ እገዳ ጥለው የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን እገዳ አንስተውታል።