ደቡብ አፍሪካ የተጣለብኝ የጉዞ ክልከላ “በጉልበት የተጫነና የማይጠቅም ነው” ስትል ተቃወመች
በደቡብ አፍሪካ 'ኦሚክሮን' የተባለ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ በርካታ ሀገራት የጉዞ እገዳ እያደረጉ ነው
የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚኒሰትር አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ተከትሎ እየተጣለ ያለው እገዳ “ሳይሳዊ አይደለም” ብለውታል
ደቡብ አፍሪካ አዲስ የተገኘውን የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ተከትሎ ሀገራት እየጣሉ ያሉት የጉዞ ክልከላ “በጉልበት የተጫነ የማይጠቅም ነው” ሰትል ተቃወመች
የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ጆ ፋህላ፤ በደቡብ አፍሪካም ሆነ በተወሰኑ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ /ሳድክ/ አባል ሀገራት ላይ የተጣለው የጉዞ እገዳ “የጉልበት ምላሽ የታከለበትና በሳይንስ ያልተደገፈ እርምጃ ነው” ብለውታል።
ሚኒሰትሩ ፋህላ፤ በበይነ መረብ አማካኝነት ለሚድያዎች በሰጡት ማብራርያ “እርምጃው ሳይንሳዊ አይመስልም፤ የጉልበት እና የፍርሃት ምላሽ ነው” ብለዋል።
በዚህ ሳምንት በደቡብ አፍሪካ አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ በርካታ ሀገራት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ጉዞ ማገዳቸው የሚታወቅ ነው።
የተወሰዱት የእገዳ እርምጃዎች "የማይጠቅሙ" ናቸው ያሉት ሚኒሰትሩ፤ ሀገራት ሌላውን ከመወንጀል በዘለለ ወረርሺኙን መከላከል ላይ ለመተባበር እንዲሰሩም ጠይቀዋል።
ፋህላ አክለው “የተጣለው የጉዞ እገዳ ገንቢ ያልሆነ ነው፤ እንዲሁም ሌሎች ሀገራት መረጃን ለመለዋወጥ ፈቃደኛ እንዳይሆኑ የሚያደርግም ነው”ብሏል።
ሌላው ከሚኒስትሩ ጋር ማብራርያ የሰጡት ፕሮፌሰር ላን ሳኔ በበኩላቸው አ”ዲሱ የኮቪድ ዝርያ በከፍተኛ ሁኔታ በሀገሪቱ እየተሰራጨ መሆኑ” ያሳስባል።
“አዲሱ ዝርያ በመላ ሀገሪቱ ተሰራጭቷል፤ ቫይረሱ በይበልጥ ሊተላለፍ የሚችል እንደሚችል እያስተዋልን ያለ ነው” ሲሉም አስታውቀዋል።
አሁን እየተነጋገርን ያለነው በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተለይተው የሚታወቁ ቢሆንም፤ ከፍተኛ ጭማሪ እያየን ነው" ብለዋል ፕሮፌሰሩ።
የዓለም ጤና ድርጅት በደቡብ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውን አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ “አሳሳቢ ዝርያ” በሚል መድቦታል።
ድርጅቱ አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ዝርያ 'ኦሚክሮን' የሚል ስያሜ እንደሰጠውም ገልጿል።
በደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 2 ሺ 828 አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ሲገኙ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በሀገሪቱ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሚልየን 955 ሺ 328 እንደደረሰም የደቡብ አፍሪካ ተላላፊ በሽታዎች ብሔራዊ ተቋም መረጃዎች ያመለክታሉ።