ደቡብ አፍሪካ እስካሁን ከ2.7 ሚልዮን በላይ የኮሮናቫይረስ ህሙማንን የመዘገበች ሀገር መሆኗ ይታወቃል
የደቡብ አፍሪካ ተመራማሪዎች አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ አገኙ፡፡አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ ተመራማሪዎች በቅርበት እየተከታተሉት ነው ተብሏል።
በተደጋጋሚ የመለዋወጥ ባህርይ ያሳያል የተባለውና C.1.2 የተባለው ይህ ዝርያ እስካሁን ድረስ ባለው ስለ አስጊነቱ ግልጽ የሆነና የታወቀ ነገር እንደሌለም ነው የደቡብ አፍሪካው የተላላፊ በሽታዎች ብሔራዊ ተቋም (ኤን.አይ.ሲዲ) የገለጸው።
በዚህ ዝርያ ተያዙ የተባሉ ሰዎች በመላው ደቡብ አፍሪካ ግዛቶች፣ በሰባት አፍሪካ አገራት፣ በእስያ፣ በአውሮፓና በኦሺኒያ እንሚገኙም ተገልጿል።
ሳይንቲስቶች ይህ ዝርያ ለኮሮናቫይረስ 'አንቲ ቦዲስ' ምን አይነት ባህርይ እንዳለውም እየተጠና ነው።በኤን.አይ.ሲዲ ተመራማሪ የሆኑት ፔኒ ሞሬ “አሁን ባለበት ደረጃ ፣ከፀረ -ተሕዋስያን ተጋላጭነት አንፃር እንዴት እንደሚሰራ ለማረጋገጥ የሚስችል የሙከራ መረጃ የለንም”ም ብሏል፡፡
ተመራማሪው ዝርያው ያለው የተለዋዋጭነት ባህርይ እንዲሁም ስለ ስርጭቱም ሌሎች ጥናቶች እየተደረገ መሆኑም ገልጿል።በዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ -19 የቴክኒክ መሪ የሆኑት ማሪያ ቫን ከርክሆቭ እንደሚሉት ዝርያው እስካሁን ባለው "በስርጭቱ ከፍ ያለ አይመስልም" ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የዴልታ ዝርያ የዋነኝነቱን ስፍራ የያዘ ሲሆን ይህ ሁኔታ ከተለወጠ የዓለም የጤና ድርጅት ለህዝቡ ያሳውቃል ብለዋል።ደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ በሚተላለፉት የዴልታ እና ቤታ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች በወረርሽኙ ክፉኛ ተመትታለች።
ሀገሪቱ እስካሁን ከ 2.7 ሚልዮን በላይ የኮሮናቫይረስ ህሙማንን የመዘገበች ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 81,830 ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል።